Skip to main content
x

የግል ባንኮች በዘጠኝ ወራት ውስጥ 8.4 ቢሊዮን ብር አተረፉ

በኢትዮጵያ የተከሰተው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት በኢኮኖሚው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሲያሳርፍ ቆይቷል፡፡ ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ምን ያህል እንደሆነ በመጠን ተተንትኖ ሲቀርብ ባይታይም፣ በችግሩ ሳቢያ ግን በርካታ የንግድ እንቅስቃሴዎች መቀዛቀዛቸው  ታይቷል፡፡ አለመረጋጋቱ የፋይናንስ እንቅስቃሴዎችንም ነካክቷል፡፡

የአዋሽ ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት አዲሱ የዘመን ባንክ ፕሬዚዳንት ሊሆኑ ነው

የዘመን ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ በሥራ ላይ ያሉትን የባንኩን ፕሬዚዳንት ለመተካት የተለያዩ ባለሙያዎችን ካወዳደረ በኋላ፣ የአዋሽ ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩትን አቶ ደረጀ ዘበነን መረጠ፡፡ የዕጩውን ፕሬዚዳንት ሹመት ለማፀደቅ ለብሔራዊ ባንክ የቀረበው ጥያቄ አዎንታዊም ምላሽ ማግኘቱ ተገለጸ፡፡

አዋሽ ባንክ ለራያ ቢራ አክሲዮኖች ግዥ የሚውል 750 ሚሊዮን ብር ብድር ለቢጂአይ ፈቀደ

አዋሽ ባንክ ቢጂአይ ኢትዮጵያ ለራያ ቢራ አክሲዮኖች ግዥ ለሚያውለው ክፍያ 750 ሚሊዮን ብር ብድር መፍቀዱ ታወቀ፡፡ የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት፣ አዋሽ ባንክ ለቢጂአይ ኢትዮጵያ የፈቀደው ብድር መጠን በአገሪቱ በግል ባንክ ለአንድ ፕሮጀክት በአንድ ጊዜ የተፈቀደ ከፍተኛው ነው፡፡ ቢጂአይ ኢትዮጵያ በቅርቡ የራያ ቢራ አክሲዮኖችን ለመግዛት ላደረገው ስምምነት ክፍያ ለመፈጸም እንዲችል ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ባንኩ ብድሩን ፈቅዷል፡፡ ቢጂአይ ኢትዮጵያ በራያ ቢራ ውስጥ ካለው የ42 በመቶ ድርሻው በተጨማሪ፣ ቀሪዎቹን አክሲዮኖች ለመግዛት ከ2.5 ቢሊዮን ብር በላይ መክፈል ይጠበቅበታል፡፡

አዋሽ ባንክ በ22.3 ሚሊዮን ብር ዕዳ ተከሰሰ

አዋሽ ባንክ በልደታ ክፍለ ከተማ ውስጥ ላስገነባውና ‹‹ባልቻ አባ ነፍሶ ቅርንጫፍ›› የሚል ስያሜ የሰጠውን ሕንፃ ለገነባለት ኮንትራክተር ከ22.3 ሚሊዮን ብር በላይ ክፍያ ባለመፈጸሙ፣ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ተመሠረተበት፡፡ ኮንትራክተሩ ጊጋ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሁለት መሠረት ያለው ባለ አሥር ፎቅ ሕንፃ ለመገንባት፣ ከአዋሽ ባንክ ጋር ሰኔ 14 ቀን 2004 ዓ.ም. ውል ተፈራርመዋል፡፡

አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ ስድስት ቢሊዮን ብር ሊያሳድግ ነው

የአዋሽ ባንክ ባለአክሲዮኖች የባንኩን ካፒታል ከሦስት ቢሊዮን ብር ወደ ስድስት ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ዛሬ ኅዳር 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በተካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ወሰኑ፡፡ ይህም በአገሪቱ ካሉት 16 የግል ባንኮች ከፍተኛው ነው፡፡