Skip to main content
x

የኢትዮ ጂቡቲ ኮሪደር መንገድ በመበላሸቱ የተሽከርካሪዎች ምልልስ እየተስተጓጎለ ነው

ከሌሎች ጎረቤት አገሮች አንፃር ሲታይ ለመሀል ኢትዮጵያ ቅርብ የሆነው የጂቡቲ ወደብ ቢሆንም፣ በተለይ ከወደቡ እስከ ጋላፊ ድረስ ያለው 200 ኪሎ ሜትር መንገድ በመበላሸቱ፣ የተሽከርካሪዎችን ምልልስ ከማስተጓጎሉም በላይ፣ ለአላስፈላጊ የመለዋወጫ ዕቃዎች ወጪ እያደረጋቸው መሆኑን ባለንብረቶች አስታወቁ፡፡

የአገሪቱን የገቢ ዕቃዎች እንደታቀደው ማስገባት አልተቻለም ተባለ

የአገሪቱን የዘጠኝ ወራት የትራንስፖርት ጉዳዮች የተመለከቱ አፈጻጸሞችን ለሕዝብ ክንፍ በማስመደጥ ውይይት ያደረገው የትራንስፖርት ሚኒስቴር፣ ካቀረባቸው ጉዳዮች አንዱ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችና ጭነቶችን የተመለከተው ይገኝበታል፡፡

የግል አቪዬሽን ኩባንያዎች ተሽከርካሪዎቻቸው የአሥር ሚሊዮን ዶላር መድን እንዲገቡ መጠየቃቸውን ተቃወሙ

የዘጠኝ ወራት የዘርፉን አፈጻጸም ለመምከር የትራንስፖርት ሚኒስቴር በጠራው ስብሰባ ላይ የግል አቪዬሽን ኦፕሬተሮች ያደረባቸውን ቅሬታ አሰሙ፡፡ አውሮፕላኖች በሚንቀሳቀሱበት ወይም በምድረ አየር ክልል (በበረራ መነሻና ማረፊያ) ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች፣ የአሥር ሚሊዮን ዶላር የመድን ሽፋን ግቡ መባላቸውን ተቃውመዋል፡፡ የትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታዎች በቀረበው ቅሬታ ላይ እንደሚነጋገሩበት አስታውቀዋል፡፡

ሶማሊያ ቅሬታዋን ኢትዮጵያ ማስተባበያዋን ያስተጋቡበት የበርበራ ወደብ የዓረብ ሊግ እንዲገባበት ጥሪ ቀረበ

የግዛቴ አካል ከሆነውና ራሱን ነፃ መንግሥት ብሎ ከሚጠራ አካል ጋር የተደረገ ስምምነት ሉዓላዊነቴን ተጋፍቷል በማለት ቅሬታውን ያሰማው የሶማሊያ መንግሥት፣ ኢትዮጵያ ከዱባዩ ዲፒ ወርልድ ኩባንያና ከሶማሌላንድ ጋር ያደረገችው የበርበራ ወደብ የባለድርሻነት ስምምነት ውድቅ እንዲደረግ ለዓረብ ሊግ ጥሪ አቀረበ፡፡

የድሮን መመርያ እየተዘጋጀ ነው

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን እያደገ የመጣውን የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር የሚያስችል፣ የድሮን መመርያ በማዘጋጀት ላይ እንደሆነ አስታወቀ፡፡ የድሮን ቴክኖሎጂ አዲስ በመሆኑ ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ አገሮች የድሮን ሕግ የላቸውም፡፡ ድሮኖች አነስተኛና በቀላል ዋጋ የሚገዙ በመሆናቸው በማንኛውም ግለሰብ እጅ እየገቡ ነው፡፡ ድሮን ለስለላ፣ ለውጊያ፣ ለቅኝት ፎቶግራፍና ለቪዲዮ ቀረፃ፣ ለመድኃኒትና የሕክምና አገልግሎቶች አቅርቦትና ለመሳሰሉት አገልግሎቶች ይውላል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት የጋራ የአየር ትራንስፖርት ገበያ ሊመሠርት ነው

የአፍሪካ አገሮች የገበያ ክልከላን በማስወገድ የጋራ የሆነ የአፍሪካ የአየር ትራንስፖርት ገበያ ሊመሠርቱ ነው፡፡ የአፍሪካ የጋራ የአየር ትራንስፖርት ገበያ በይፋ የሚመሠረተው፣ ጥር 20 ቀን 2010 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በሚካሄደው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ነው፡፡ የአፍሪካ የአየር ትራንስፖርት ገበያ በክልከላ የተተበተበ በመሆኑ፣ የአፍሪካ አየር መንገዶች አፍሪካ ውስጥ እንደልባቸው መሥራት ተስኗቸው እንደቆየ የአቪዬሽን ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ የአፍሪካ አገሮች ለአፍሪካ አየር መንገዶች የበረራ ፈቃድ ለመስጠት ሲያንገራግሩ ይታያል፡፡ በዚህም ምክንያት የአፍሪካ አገሮች በአየር ትራንስፖርት ያላቸው ትስስር ዝቅተኛ እንደሆነ ይነገራል፡፡፡

የግል ትራንስፖርት ኩባንያዎች በመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓት እንዲሰማሩ ጥያቄ ቀረበ

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የግል የትራንስፖርት ኩባንያዎች፣ በመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓት እንዲሳተፉ ጥያቄ አቀረበ፡፡ የሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ከማሪታይም ባለሥልጣን ጋር በጋራ በመሆን ባደረጉት ጥናት፣ በጂቡቲ ወደብ ለበርካታ ቀናት ተከማችተው የሚቆዩ የአገሪቱ ንብረቶች በፍጥነት መነሳት አለባቸው፡፡ በኮንቴይነር ታሽገው ከሚቀርቡ ንብረቶች ውጪ ያሉ ሌሎች ዕቃዎችም በመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓት ወደ አገር ውስጥ መግባት እንዳለበት ተስማምተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለጂቡቲ የምትሰጠው ንፁህ ውኃ በሦስት ወራት ውስጥ እንደሚሠራጭ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ለጂቡቲ በነፃ የምትሰጠው የንፁህ ውኃ አቅርቦት ግንባታው ተጠናቆ፣ በሦስት ወራት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ለጂቡቲያውያን መዳረስ እንደሚጀምር ተገለጸ፡፡ በጂቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሻሜቦ ፊታሞ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት፣ በጂቡቲ መንግሥት ወጪ የተካሄደው የንፁህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ግንባታ አብዛኛው ሥራው ተጠናቋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የጂቡቲ ከተሞች በመጠኑ የውኃ ሥርጭቱ መጀመሩም ተጠቅሷል፡፡

ከጂቡቲ ኢትዮጵያ ሊዘረጋ የታሰበው የነዳጅ መስመር ፕሮጀክት ታጠፈ

ኢትዮጵያ በከፍተኛ ወጪ ከጂቡቲ ወደብ ወደ መሀል አገር የምታስገባው የተጣራ የነዳጅ ውጤቶች ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ፕሮጀክት እንደታጠፈ ታወቀ፡፡ ተቀማጭነቱ በደቡብ አፍሪካ የሆነው ብላክ ራይኖ የተባለ ኩባንያ ከጂቡቲ ወደብ አዋሽ አርባ የሚገኘው የነዳጅ ዴፖ የሚደርስ 550 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ ለመዘርጋት የሚያስችል ዕቅድ፣ ለኢትዮጵያ መንግሥት ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

የኮሪያ መንግሥት ለኢትዮጵያ የፍጥነት መንገዶች ግንባታ ድጋፍ እንደሚሰጥ አስታወቀ

የደቡብ ኮሪያ መንግሥት በኢትዮጵያ እየተገነቡ ለሚገኙና ወደፊት እንደሚገነቡ ለሚታሰቡ የመንገድ መሠረተ ልማቶች ድጋፍ የመስጠት ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ፡፡ በአዳዲስ መንገዶች ግንባታ ለመሳተፍ የኮሪያ መንግሥት ኩባንያ ከመንግሥት ጋር ድርድር ጀምሯል፡፡