Skip to main content
x

ትጥቅ የመፍታት አተካራና የመንግሥት ተገዳዳሪነት

ሐሙስ ጥቅምት 8 ቀን 2011 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮችና በፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ላይ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) ባሰሙት ንግግር ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በፓርላማ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ ለተጠየቋቸው አሥር ጥያቄዎች መልስ ሲሰጡ ካነሷቸው ነጥቦች አንዱ በአንድ አገር ውስጥ በቡድን የመታጠቅ መብት ያለው መንግሥት ብቻ ነው የሚለው ነበር፡፡

ውዥንብሮች ትርምስ እየፈጠሩ አገር አይታመስ!

ፈጣን፣ ቀልጣፋና ውጤታማ የመረጃ ልውውጦች ባለመኖራቸው ምክንያት ግልጽነት የጎደላቸው በርካታ ድርጊቶች ይስተዋላሉ፡፡ አንድ ብሔራዊ ጉዳይ ሲያጋጥም በቀጥታ የሚመለከተው መንግሥታዊ አካል በፍጥነት መረጃ ስለማይሰጥ፣ አገር ምድሩ በአሉባልታና በመሠረተ ቢስ ወሬዎች ይጥለቀለቃል፡፡

የመከላከያ አባላት የጥቅማጥቅም ጥያቄ በአዲስ አበባ ጊዜያዊ ውጥረትን ፈጠረ

ዛሬ መስከረም 30 ቀን 2011 ዓ.ም. የተለያዩ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ተወካዮች የጥቅማጥቅምና የደመወዝ ማስተካከያ ይደረግልን በማለት ከካምፕና ከሚሠሩበት ሥፍራ በመውጣት በጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ አካባቢ ጥያቄያቸውን አቀረቡ፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአዲስ ዓመት ውሎ በቡሬና በዛላምበሳ ግንባሮች

ማክሰኞ መስከረም 1 ቀን 2011 ዓ.ም. በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ከፍተኛ ጦርነት በተካሄደባቸው በቡሬና በዛላምበሳ ግንባሮች ከሁለቱ አገሮች የመከላከያ ሠራዊቶችና ከአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ጋር የአዲስ ዓመት በዓል ያሳለፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ጦር ውጥረት ከነገሠባቸው የድንበር አካባቢዎች እንዲነሳ መወሰኑን አስታወቁ፡፡

በደቡብ ክልል ብጥብጦች ያጎሉት የክልልነት ጥያቄ

ባለፉት ሦስት ዓመታት በበርካታ የአገሪቱ ክፍሎች ሰፋፊ ሁከቶች፣ ተቃውሞዎችና አመፆች በነበሩበት ጊዜ የደቡብ ክልል ከተወሰኑ አካባቢዎች በስተቀር በአብዛኛው ሰላማዊ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ በወቅቱ በተለይ በኮንሶና በሰገን ሕዝቦች ዞኖች አካባቢ ከታዩ ግጭቶች በላይ ጎልቶ የወጣ ግጭት በክልሉ አልተስተዋለም ነበር፡፡

መንግሥት ኢትዮጵያ ጦሯን ከኤርትራ ድንበር አለማንሳቷን አስታወቀ

ኢትዮጵያ ጦሯን ከኤርትራ ድንበር እያነሳች ነው ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ሐሰት ነው ሲል መንግሥት አስተባበለ፡፡ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አካባቢ በኢትዮጵያና በኤርትራ ድንበር በተለይም በሽራሮ ግንባር የሚገኘው ጦሯን ኢትዮጵያ እያነሳች እንደሆነ፣ በርካታ ቁጥር ያላቸው አውቶብሶችና ኦራል ወታደራዊ የጭነት ተሽከርካሪዎች ጦሩን ሲያጓጉዙ መታየታቸውን፣ በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያዎች ሲሰራጭ ነበር፡፡

በጅግጅጋና በሌሎች የሶማሌ ክልል ከተሞች የተቀሰቀሰው ግጭት የፈጠረው ውጥረት

ቅዳሜ ሐምሌ 28 ቀን 2010 ዓ.ም. በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የተቀሰቀሰው ግጭት በቀብረ ደሃር፣ በጎዴና በደገሃቡር ከተሞችም በመስፋፋት የክልሉ ብሔር አባላት ባልሆኑ ነዋሪዎች ላይ ያነጣጠረ ጉዳት ደርሷል፡፡

በሶማሌ ክልል በተፈጠረው ቀውስ የነዳጅ ኩባንያዎች ሥራ አቋርጠዋል

በሶማሌ ክልል በተፈጠረው የፖለቲካና የፀጥታ ቀውስ ሥጋት የገባቸው በክልሉ የነዳጅ ፍለጋ ሥራ የሚያካሂዱ ኩባንያዎች ሥራ ማቋረጣቸው ታወቀ፡፡ በክልሉ በተፈጠረው የፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት ከሐምሌ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በክልሉ ዋና ከተማ ጅግጅጋና ሌሎች አነስተኛ ከተሞች በተፈጠሩ ግጭቶች በርካታ ሰላማዊ ዜጎች መገደላቸው፣ የንግድና የመኖሪያ ቤቶች፣ ባንክና ቤተ ክርስቲያኖች መዘረፋቸውና መቃጠላቸው የሚታወስ ነው፡፡