Skip to main content
x

አገር በቀል ድርጅት የኢትዮጵያ ጠለፋ ዋስትና ኩባንያ የሰው ሀብት ስትራቴጂ ለመሥራት ጨረታ አሸነፈ

የተባለ አገር በቀል ድርጅት ከሁለት ዓመታት በፊት ለተቋቋመው የኢትዮጵያ ጠለፋ ዋስትና አክሲዮን ማኅበር፣ የሰው ሀብት ስትራቴጂ ለማዘጋጀት የወጣውን ጨረታ በ2.1 ሚሊዮን ብር አሸነፈ፡፡ ጨረታውን ያሸነፈው ከታዋቂው የሆላንድ ኩባንያ ጋር ተወዳድሮ ነው፡፡

የመሬት ሊዝ ጨረታ በግርግር ታጅቦ ተከፈተ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ራሱ ባበለፀገው አዲስ ሶፍትዌር ታግዞ ይፋ ያደረገው 29ኛው የመሬት ሊዝ ጨረታ በግርግር ታጅቦ ተከፈተ፡፡ ጨረታው ለአንድ ካሬ ሜትር መሬት ዝቅተኛው 12 ሺሕ ብር ከፍተኛው 100 ሺሕ ብር የመወዳደሪያ ዋጋ ቀርቧል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከዘጠኝ ወራት በኋላ የመሬት ሊዝ ጨረታ አወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየወሩ የመሬት ሊዝ ጨረታ እንደሚያወጣ ቢደነግግም፣ የበጀት ዓመቱ ሊጠናቀቅ አንድ ወር ያህል ሲቀረው በጉጉት ሲጠበቅ የቆየውን 29ኛውን የሊዝ ጨረታ አወጣ፡፡ 29ኛው የሊዝ ጨረታ ከዚህ ቀደም የተለመደው ልማዳዊ አሠራር እንደማይኖር፣ ይልቁንም አስተዳደሩ ባበለፀገው አዲስ ሶፍትዌር ጥቅም ላይ እንደሚውል ተገልጿል፡፡

ለስንዴ እጥረት ምክንያት የሆነው ዓለም አቀፍ ግዥ አወዛጋቢ ሆኖ ቀጥሏል

ለአገራዊ የስንዴ እጥረት መፈጠር ምክንያት የሆነው የ400 ሺሕ ቶን ስንዴ ግዥ አሁንም አወዛጋቢ ሆኖ ቀጥሏል፡፡ ስድስት ወራት ሙሉ የተጓተተው የስንዴ ጨረታ ገዥውን አካል ማለትም የመንግሥት ግዥዎችና ንብረት ማስወገድ አገልግሎትን ለወቀሳ ዳርጎታል፡፡ ከዚህ ቀደም ጨረታው በወጣበት ጊዜ ሻኪል የተባለ የፓኪስታን ኩባንያ 2.6 ቢሊዮን ብር ዝቅተኛ ዋጋ በማቅረብ ጨረታውን አሸንፎ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ዳቦ ያሳጡ አንጀት ይልጡ

መንግሥት መሠረታዊ የሚባሉ እንደ ስንዴ፣ ዱቄት፣ ዳቦ፣ ዘይትና ስኳር የመሳሰሉት ምርቶችን ሥርጭትና ግብይት በመቆጣጠር እንዲገበያዩ ያደርጋል፡፡  ይህን የሚያደርገውም እንዲህ ያሉትን መሠረታዊ ሸቀጦች በዋጋ እየደጎመ ማቅረቡን በመከራከሪያነት በማቅረብ ነው፡፡ ለዓመታት በዚህ መንገድ ሲሠራ ቆይቷል፡፡ ይህ የድጎማ አሠራር በዚህ መንገድ እንዲካሄድ ታምኖበት እየተተገበረ ይገኛል፡፡

የሒልተን ሆቴል ሽያጭ ዋጋ ትመና ጥናት ተጠናቀቀ

የሒልተን አዲስ አበባ ሆቴልን ወደ ግል ይዞታ ለማዘዋወር ሲደረግ የነበረው የዋጋ ትመና ጥናት መጠናቀቁን ታወቀ፡፡ የዋጋ ትመና ጥናቱን ሲያካሄድ የነበረው የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የተባለ መንግሥታዊ አማካሪ ተቋም ጥናቱን አጠናቆ፣ ለመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር ማቅረቡን የሪፖርተር ምንጮች ተናግረዋል፡፡

ብሔራዊ አልኮል ፋብሪካን ወደ ግል ይዞታ ለማዛወር ጨረታ ወጣ

የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር የብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካን ሙሉ በሙሉ ወደ ግል ይዞታ ለማዛወር ጨረታ አወጣ፡፡ ፋብሪካው ሚኒስቴሩ ወደ ግል ይዞታ ሙሉ በሙሉ ለማስተላለፍ ካቀዳቸው ድርጅቶች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ከፍተኛ ሽያጭና ትርፍ በማስመዝገብ ስኬታማ እንደሆነ የሚታወቀው ይህ ፋብሪካ፣ በአሁኑ ጊዜ ከ42 በመቶ በላይ የሚሆነውን የአገሪቱን የአረቄ ገበያ እንደተቆጣጠረ ይነገርለታል፡፡

ለ29ኛው የመሬት ሊዝ ጨረታ አዲስ ሶፍትዌር እየተዘጋጀ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየወሩ መሬት በሊዝ ለማስተላለፍ ጨረታ እንደሚያወጣ ቢደነግግም፣ ላለፉት ሰባት ወራት አንድም ጊዜ ጨረታ አላወጣም፡፡ የአዲስ አበባ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ጨረታ ማውጣት ያልቻለው፣ ጨረታውን ግልጽ ለማድረግ ዘመናዊ አሠራር ተግባራዊ ማድረግ በማስፈለጉ ነው ብሏል፡፡ ለዚህም ሲባል አዲስ ሶፍትዌር እየተዘጋጀ መሆኑ ታውቋል፡፡  

ለአርሶ አደሮች የሚቀርበው ማዳበሪያ ላይ የዋጋ ጭማሪ ተደረገ

በዓለም አቀፍ ገበያ ከዩሪያ በስተቀር በሌሎች የማዳበሪያ ዓይነቶች ላይ  የዋጋ ጭማሪ ባይደረግም፣ ብር ከዶላር ጋር ያለው ምጣኔ በ15 በመቶ እንዲቀንሰ በመደረጉ ምክንያት ለአርሶ አደሮች በሚቀርበው ማዳበሪያ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ፡፡

ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ የ40/60 ሱቅ ለመግዛት ከ26 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ አቀረበ

ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ የአዲስ አበባ ከተማ የቁጠባ ቤቶች ኢንተርፕራይዝ የንግድ ቤቶችን ለመሸጥ ባወጣው ጨረታ፣ 156 ካሬ ሜትር የ40/60 ሱቅ ለመግዛት 26.6 ሚሊዮን ብር የመጫረቻ ዋጋ አቀረበ፡፡ ባንኩ የሰጠው ዋጋ ለሁሉም ሱቆች ከተሰጡት ዋጋዎች በከፍተኛነት ተመዝግቧል፡፡