Skip to main content
x

ረሃብን በ2030 ዜሮ ለማድረግ

ረሃብን በዓለም አቀፍ ደረጃ እ.ኤ.አ. በ2030 ለማጥፋት አገሮች፣ የተባበሩት መንግሥታት የምግብና የእርሻ ድርጅት እንዲሁም በዘርፉ የተሰማሩ አካላት መረባረብ ከጀመሩ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በዚህም በየአገሮች መሻሻሎች እየታዩ፣ ምርትና ምርታማነት እየጨመረ፣ ረሃብን የማጥፋት ዘመቻው እየጎለበተና ረሃብ እየቀነሰ መጥቶ የነበረ ቢሆንም፣ ረሃብ መልሶ እያገረሸ ነው፡፡

‹‹ግብርናውን ለማበልፀግ ቴክኖሎጂዎችን ከነምክረ ሐሳባቸው አሟልቶ መተግበር ያስፈልጋል››

በግብርናው ዘርፍ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በግብርናው ዘርፍ ያሉ ምርምሮች አዎንታዊ ሚና አላቸው፡፡ ከ50 ዓመታት በፊት የተቋቋመው የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩትም የግብርናውን ዘርፍ ለማበልፀግ የተለያዩ የምርምር ሥራዎችን በየጊዜው ያወጣል፡፡ አቶ ፍሥሐ ዘገየ፣ በግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የግብርና ኤክስቴንሽን ተመራማሪ ናቸው፡፡

የትራኮማውን ጫና ለማርገብ

ፍሬድ ሃውሎስ ፋውንዴሽን መቀመጫውን በአውስትራሊያ ያደረገ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች መከላከል በሚቻሉ ሕመሞች የሚመጣውን ዓይነሥውርነት ለመግታት ይሠራል፡፡ በኢትዮጵያም ከ100 ሺሕ ለሚልቁ የትራኮማ ሕሙማን ቀዶ ሕክምና አድርጓል፡፡

ማማከርና ምርምርን ለውጭ ምንዛሪ ምንጭነት

ዶ/ር ማርቆስ ፈለቀ የኤቢኤች ፓርትነርስ መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ናቸው፡፡ የአንደኛና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የተከታተሉት ተወልደው ባደጉበት ቢሾፍቱ ከተማ ነው፡፡ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ በኅብረተሰብ አቀፍ ሕክምና የመጀመርያ ዲግሪ፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በፐብሊክ ሔልዝ ላይ ሠርተዋል፡፡

ከአብነት ትምህርት ቤት የፈለቀው ዩኒቨርሲቲ

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በ1935 ዓ.ም. ለመጀመርያ ጊዜ ካህናትንና የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትን ዘመናዊውንና የአብነት ትምህርታቸውን አስተባብረው እንዲይዙና ማኅበረሰባቸው በዕውቀት እንዲያገለግሉበት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከግላቸው የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ እንደ ነበር ያስረዳል፡፡

የብርሃን ለሕፃናት ስኬቶች

ወ/ሮ እቴነሽ ወንድማአገኘሁ በሕፃናት አካል ጉዳተኞች ዙሪያ የሚሠራ ‹‹ብርሃን ለሕፃናት›› የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ ናቸው፡፡ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በዳግማዊ ምኒልክ መሰናዶ ትምህርት ቤት ካጠናቀቁ በኋላ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሶሻል ወርክ የመጀመርያና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ሠርተዋል፡፡

‹‹እኛ ቢሮ ኩላሊት መሸጥ እንፈልጋለን የሚሉ በርካታ ወጣቶች ይመጣሉ››

የኩላሊት ሕመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት ከተመሠረተ ሰባት ዓመታት አስቆጥሯል፡፡ ድርጅቱን የመሠረቱት 43 ታማሚዎች አንድ ላይ በመሆን ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት አብዛኞቹ መሥራቾች ሞተው በሕይወት የቀሩት አንዱ ብቻ ናቸው፡፡

‹‹የኢትዮጵያን ችግር ለመቅረፍ ኢትዮጵያዊ ሥርዓተ ትምህርት ያስፈልጋል››

ዶ/ር ዳምጠው ወልደ ማርያም የጃፓይጎ ከሚተገብራቸው ፕሮጀክቶች መካከል የሆነው በጤናው ዘርፍ የሰው ሀብት ልማት ላይ አተኩሮ የሚሠራው ፕሮጀክት ዳይሬክተር ናቸው፡፡ ጃፓይጎ መቀመጫውን በባልቲሞር ያደረገ የጆንሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ አካል የሆነ ግብረ ሰናይ ተቋም ነው፡