Skip to main content
x

ለአዲስ አበባ ከተማ ንፁህ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክት የውጭ ምንዛሪ ተፈቀደ

የአዲስ አበባ ከተማን ንፁህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ለማሻሻል ከተጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች አንዱ ለሆነው ኖርዝ አያት ፋንታ ጥልቅ ውኃ ፕሮጀክት የሚያስፈልጉ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ዕቃዎች ግዥ ለመፈጸም የውጭ ምንዛሪ እንዲፈቀድ በተደጋጋሚ ቢሞከርም ምላሽ ሳያገኝ ቆይቶ፣ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አዲሱ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) እና አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) ባካሄዱት ውይይት የውጭ ምንዛሪ መፈቀዱ ታወቀ፡፡

ባንኮች በሁለት ሳምንት ውስጥ ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ መንዝረዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በቅርቡ የውጭ ገንዘብ በእጃቸው የሚገኝ ዜጎች ወደ ባንክ እንዲያስገቡ ማሳሰባቸው ይታወሳል፡፡ ይህንኑ ተከትሎም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የግል ባንኮች ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ በሁለት ሳምንት ውስጥ እንደመነዘሩ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ጉዳይ

ባለፉት ሦስት ዓመታት በኢትዮጵያ ያጋጠመው ከፍተኛ አመፅና የፖለቲካ አለመረጋጋት የሰዎችን ሕይወት ከመቅጠፍና ንብረት ከማውደም ባለፈ፣ በኢኮኖሚው ላይ ያደረሰው ጉዳት ባይለካም እጅግ ከፍተኛ እንደነበረ መገመት አይከብድም፡፡

ናሽናል ሲሚንቶ ወደ ውጭ ከላከው ምርት ከ17 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አስመዘገበ

በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች የሚሳተፈውና የኢስት አፍሪካ ሆልዲንግ የእህት ኩባንያ የሆነው ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ፣ ምርቱን ለውጭ ገበያ በማቅረብ ያገኝ የነበረውን የውጭ ምንዛሪ ከእጥፍ በላይ በማሳደግ ከ17 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማግኘቱ ተገለጸ፡፡

የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓት አምራቾች በውጭ ምንዛሪ እጥረት መማረራቸውን ገለጹ

የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ልማት ኢንስቲትዩት ከባለድርሻ አካላት ጋር ሐምሌ 6 ቀን 2010 ዓ.ም. በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ባካሄደው የውይይት መድረክ፣ ባለሀብቶች የውጭ ምንዛሪ እጥረት እንዳማረራቸው አስታወቁ፡፡

መንግሥት ጣልቃ ካልገባ በስተቀር አዲስ አበባ በውኃ እጥረት እንደምትመታ ማስጠንቀቂያ ተሰጠ

የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አወቀ ኃይለ ማርያም (ኢንጂነር)፣ በአገሪቱ የሚገኙ ባንኮች ለውኃ ፕሮጀክቶች የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት ተገቢውን ትኩረት በመንፈጋቸው ከአንድ ዓመት በኋላ ከተማው ከፍተኛ የውኃ እጥረት ሊያጋጥመው እንደሚችል አስጠነቀቁ፡፡

ለወጪ ንግዱም ፖሊሲ ይውጣለት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አሕመድ ወደ ኃላፊነታቸው ከመጡ ወዲህ ለፈጸሟቸው መልካምና ተስፋ ሰጪ ተግባራት ባልተለመደ መልኩ ምሥጋና ለማቅረብ መስቀል አደባባይ በነቂስ የወጣው ሕዝብ ላይ የደረሰው የቦምብ አደጋ አስደንጋጭ ነበር፡፡