Skip to main content
x

ንግድ ሚኒስቴር አወዛጋቢ የነበሩ ሁለት መመርያዎችን አሻሻለ

ንግድ ሚኒስቴር አወዛጋቢ ሆነው የቆዩትን የቅድመ ንግድ ፈቃድ ብቃት ማረጋገጫና የኢትዮጵያ የንግድ ሥራ ፈቃድ መስጫ መደብ መመርያዎችን አሻሻለ፡፡ እነዚህ መመርያዎች በኢትዮጵያ በቀላሉ የንግድ ሥራዎችን ለማካሄድ እንቅፋት ናቸው ተብለው በንግዱ ማኅበረሰብ ከፍተኛ ቅሬታ የሚቀርብባቸው ናቸው፡፡

ንግድ ሚኒስቴር በፓልም ዘይት ንግድ ለሚሰማሩ ረቂቅ መመርያ አዘጋጀ

ንግድ ሚኒስቴር ከውጭ ፓልም ዘይት አስመጥተው ማከፋፈል የሚፈልጉ ኩባንያዎችን ማስተናገድ የሚያስችል ረቂቅ መመርያ አዘጋጀ፡፡ በተዘጋጀው ረቂቅ መመርያ ላይ ንግድ ሚኒስቴር ከክልልና ከተማ አስተዳደር፣ ከመንግሥት፣ ከኢንዶውመንትና ከግል ድርጅቶች ጋር መክሯል፡፡

የዘጠኝ ወራት የወጪ ንግድ ገቢ 2.1 ቢሊዮን ዶላር ሆነ

ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ከወጪ ንግድ 2.1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷ ተገለጸ፡፡ ይህ ገቢ በዕቅድ ተይዞ ከነበረው 3.6 ቢሊዮን ዶላር ጋር ሲነፃፀር 57 በመቶው ብቻ እንደተሳካ ታውቋል፡፡ በተጨማሪም ካለፈው ዓመት የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ጋር ሲነፃፀር የ4.3 በመቶ (100 ሚሊዮን ዶላር) ብቻ ጭማሪ ተመዝግቧል፡፡ አብዛኛው ገቢ ከዚህ ቀደም እንደተለመደው ከግብርናው ዘርፍ የተገኘ ሲሆን፣ ቀሪው ከማኑፋክቸሪንግና ከማዕድን ዘርፍ ነው፡፡

የንግድ ሚኒስቴር የዘጠኝ ወራት ሪፖርት ዛሬ ይፋ ይደረጋል

ንግድ ሚኒስቴር የአገሪቱን አጠቃላይ የዘጠኝ ወራት የወጪና ገቢ ንግድ አፈጻጸም ሪፖርት ለማሳወቅ ለረቡዕ ግንቦት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ቀጠሮ ቢይዝም፣ ከቡና ወጪ ንግድ የተመዘገበው የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ይፋ ተደርጓል፡፡  በ2010 በጀት ዓመት ከሐምሌ እስከ መጋቢት ወራት ውስጥ የታየው የቡና የወጪ ንግድ አፈጻጸምን በማስመልከት የቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ግብይትና ልማት ባለሥልጣን ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያሳየው ለውጭ ገበያ ከቀረበው ቡና የተገኘው የውጭ ምንዛሪ ገቢ 560.24 ሚሊዮን ዶላር ነው፡፡  

ዳቦ ያሳጡ አንጀት ይልጡ

መንግሥት መሠረታዊ የሚባሉ እንደ ስንዴ፣ ዱቄት፣ ዳቦ፣ ዘይትና ስኳር የመሳሰሉት ምርቶችን ሥርጭትና ግብይት በመቆጣጠር እንዲገበያዩ ያደርጋል፡፡  ይህን የሚያደርገውም እንዲህ ያሉትን መሠረታዊ ሸቀጦች በዋጋ እየደጎመ ማቅረቡን በመከራከሪያነት በማቅረብ ነው፡፡ ለዓመታት በዚህ መንገድ ሲሠራ ቆይቷል፡፡ ይህ የድጎማ አሠራር በዚህ መንገድ እንዲካሄድ ታምኖበት እየተተገበረ ይገኛል፡፡

በፀጥታ መደፍረስ የተጎዳውን የንግድ እንቅስቃሴ የሚገመግም ጉባዔ ተጠራ

በአገሪቱ አጋጥሞ የነበረው የፀጥታ መደፍረስ በንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ ያሳደረውን ተፅዕኖ በመገምገም፣ መፍትሔ የሚያመላክት ጉባዔ በአማራ ክልል ርዕሰ ከተማ በባህር ዳር ከተማ ሊካሄድ ነው፡፡ የንግድ ሚኒስቴር ከግንቦት 8 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ቀናት በጠራው ‹‹የክልሎች መድረክ›› ጉባዔ ላይ፣ ዘጠኙ ክልሎችና ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሏል፡፡