Skip to main content
x

የአስተዳደራዊ ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ የፀደቀበት መንገድ ሕጋዊ ወይስ ፖለቲካዊ?

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ኅዳር 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባው ሁለት ኮሚሽኖችን ለማቋቋም በተረቀቁ የሕግ ሰነዶች ላይ ተወያይቶ በማፅደቅ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ረቂቅ አዋጆቹን እንዲያፀድቃቸው በላከው መሠረት ኅዳር 20 ቀን ረቂቆቹ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበዋል።

የትራንስፖርት አሠሪዎች ፌዴሬሽን ተቋቋመ

የትራንስፖርት አሠሪዎች ፌዴሬሽን መመሥረቱ ጥቅምት 1 ቀን 2011 ዓ.ም. በይፋ ተበሰረ፡፡ በካፒታል ሆቴል በተከናወነው ሥነ ሥርዓት ላይ መቋቋሙ የተበሰረው ይኼው ፌዴሬሽን ከሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሕጋዊ ዕውቅና ተችሮታል፡፡

የፌዴሬሽኑ ዕጩ ፕሬዚዳንታዊና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዝርዝር ይፋ ሆነ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሚያዝያ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. በካፒታል ሆቴል በጠራው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ የተሰየመው የፌዴሬሽኑ አስመራጭ ኮሚቴ ግንቦት 26 ቀን በአፋር ሰመራ ለሚደረገው ፕሬዚዳንታዊና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ምርጫ የሚቀርቡ ዕጩዎችን ይፋ አድርጓል፡፡ አስመራጭ ኮሚቴው ግንቦት 14 ቀን ይፋ ባደረገው ዝርዝር መሠረት ከፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የአዲስ አበባ፣ የትግራይና የጋምቤላ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች የወከሏቸው ኢንጂነር ፀደቀ ይሁኔ፣ አቶ ተስፋዬ ካህሳይና ኢንጂነር ቶል ቤል በተደረገው ማጣራት መሠረት ከዕጩነት ዝርዝር ውጪ ተደርገዋል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስና የምርጫ ጨረታ

በካምቦሎጆ ዙሪያ ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ የደራና የጦፈ የድለላ ሽሚያ የሚስተዋልበትን ክስተት ከመጋረጃ ጀርባ እያስተናገደ ይገኛል፡፡ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንታዊና የሥራ አስፈጻሚ ኮሜቴ ምርጫ ባልተከናወነበት በዚህ ወቅት፣ ጉዳዩ ለጨረታ የቀረበ እስኪመስል የተቋሙ የዋና ጸሐፊነት ቦታና ሌሎችም በንዑስ ኮሚቴ የሚመሩ ልዩ ልዩ ክፍሎች በእነማን እንደሚመሩ ከወዲሁ ለእነማን እንደሚሆን መቃወቅ የጀመረ ይመስላል፡፡

ክልሎች የዕጩዎቻቸውን ሰብዕናና ብቃት እንዲያጤኑ ተጠየቀ

ገላጋይ ሕግ አጥቶ ለወራት ሲያወዛግብ የቆየው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንታዊና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ምርጫ ለመጨረሻ ጊዜ በተባለለት ግንቦት 26 ቀን 2010 ዓ.ም. በአፋር ሰመራ ይደረጋል፡፡ ክልሎች ለምርጫው ዕጩ የሚያቀርቡበት ቀነ ገደብ ከነገ በስቲያ ዓርብ ግንቦት 10 ቀን ያበቃል፡፡ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በቅርቡ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አከናውኖ፣ ምርጫውን በሚመለከት ተፈጥሮ የቆየውን ብዥታ እንዲጠራ በማድረግ፣ አዲስ የአስመራጭ ኮሚቴ መሰየሙ አይዘነጋም፡፡

የእግር ኳሱ ጉባዔ ስያሜውን የሚመጥን ውሳኔ እንዲያሳልፍ ተጠየቀ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከዓለም አቀፍ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር (ፊፋ) የተላከውን የምርጫ ሕግ ለማፅደቅ ለቅዳሜ ሚያዝያ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. በካፒታል ሆቴል ጠቅላላ ጉባዔውን ጠርቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ጠቅላላ ጉባዔው ፊፋ ባስተላለፈው ትዕዛዝ መሠረት ቀጣዩን የፌዴሬሽኑን ፕሬዚዳንታዊና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለመምረጥ የሚያስችለውን አዲስ አስመራጭ ኮሚቴ እንደሚሰየም ይጠበቃል፡፡

የአዲሱ አስመራጭ ኮሚቴ ምርጫና ከጉባዔው የሚጠበቀው

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቀጣይ አመራርን ለመምረጥ እየተደረገ የነበረው የተንዛዛ አካሄድ ምንም እንኳ የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) መፍትሔ ያለውን የውሳኔ ሐሳብ ቢያሳልፍም፣ አሁንም መቋጫውን አላገኘም፡፡ በተለያዩ ግለሰባዊ ፍላጎቶች ፍትጊያዎችን ያስተናገደው ይህ ምርጫ ከበርካታ ባለሙያዎችና አስተያየት ሰጪዎች የሰላ ትችት ሲያስተናግድ ከርሟል፡፡

የፊፋ መልዕክተኞችና ትዝብት ውስጥ የገባው የእግር ኳሱ ምርጫ

​​​​​​​ከሰሞኑ የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) ተወካዮች በአዲስ አበባ ቆይታ አድርገው፣ የአገሪቱን የስፖርት አመራሮችና ዕጩ ተወዳዳሪዎችን አነጋግረው ተመልሰዋል፡፡ ተወካዮቹ የብሔራዊ ፌዴሬሽኑን ቀጣይ አመራሮች ለመምረጥ በነበረው ሒደት ሲከናወን የቆየውንና ያለውን ሽኩቻ ተከትሎ ለማጣራት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጣ ከተነገረ ሰነባብቷል፡፡