Skip to main content
x

ሆሄ የማኅበራዊ ድረ ገጽ ጸሐፊዎችን ያወዳድራል

ሆሄ ዓመታዊ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት ማኅበራዊ ድረ ገጾችን በመጠቀም ግጥምና ወግ የሚያስነብቡ ጀማሪ ጸሐፊዎችን አወዳድሮ እንደሚሸልም አስታውቋል፡፡ ዓምና የመጀመሪያው ዙር ውድድር የተካሄደው በረዥም ልቦለድ፣ በልጆች መጻሕፍትና በግጥም ዘርፍ ሲሆን፣ ዘንድሮ የማኅበራዊ ድረ ገጽ ታክሎበታል፡፡ በ2009 ዓ.ም. በማኅበራዊ ድረ ገጽ (በዋነኛነት በፌስቡክ) ከቀረቡ ግጥሞችና ወጎች በተጨማሪ ታትመው ለንባብ የቀረቡ የወግ መጻሕፍትም በውድድሩ ይካፈላሉ፡፡

ሁለተኛው የአፍሪካ ሰርከስ ፌስቲቫል ይካሄዳል

ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄደው አፍሪካ ሰርከስ አርትስ ፌስቲቫል ከየካቲት 23 እስከ የካቲት 25 ቀን 2010 ዓ.ም. ይካሄዳል፡፡ አዘጋጁ ፍካት ሰርከስ ለሪፖርተር በላከው መግለጫ መሠረት፣ በፌስቲቫሉ ከአሥራ አንድ የአፍሪካ አገሮች የተውጣጡ የሰርከስ ክለቦች ይገኛሉ፡፡

የኢትዮጵያና የኢራን ጥበባዊ ትስስር

የምሽቱ መርሐ ግብር የተጀመረው በመሶብ ባንድ ባህላዊ ሙዚቃዎች ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የተገኙትን ታዳሚዎች በሙዚቃዎቻቸው ዘና አድርገዋል፡፡ ባንዱ በተለይም ግጥም በጃዝ በሚቀርብባቸው የሥነ ጽሑፍ ምሽቶች በባህላዊ ሙዚቃ የግጥም ሥራዎችን በማጀብ ይታወቃል፡፡ በክራር፣ በመሰንቆ፣ በዋሽንትና በከበሮ ውህድ ግጥሞቻቸውን ያስደመጡ ጸሐፍትም በርካታ ናቸው፡፡

የመጽሐፍ ምርቃት

ዝግጅት፡- ‹‹ባለቀን›› የተሰኘው የትንቢት ምናለ የግጥም መድበል ይመረቃል፡፡ ቀን፡- የካቲት 10 ቀን 2010 ዓ.ም. ሰዓት፡- 2፡30

የቅዱስ ላሊበላ ውቅር መቅደሶችን የመታደግ ጅምር

‹‹…የምገልጽበት ቋንቋ የለኝም፡፡ የዚህን ክቡር ሰው፣ ከሁሉም መሬታውያን በጥበብም ሆነ በሥነ ጽድቅ የከበረ ላሊበላ ከአንድ ደንጊያ፣ ከአንድ አለት ፈልፍሎ ዐሥር አብያተ ክርስቲያናትን ያነፀው ዐቢይ ሥራ የምገልጽበት ልሳን የለኝም::›› ከስምንት መቶ ዓመታት በፊት በዛጒዬ ሥርወ መንግሥት ዘመን በላስታ ላሊበላ የተሠሩትን ዕፁብ ድንቅ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ያከናወናቸው የቅዱስ ላሊበላን ገድል በኋላ ዘመን ላይ የጻፈው ደራሲ ውሳጣዊ ስሜቱን የገለጸበት ነበር፡፡

የሳልሳ ሀሁ…

የአፍሪካ ሙዚቃና ባህል ልውውጥ ፌስቲቫል (አፍሪካ ሚውዚክ ኤንድ ካልቸራል ኤክስቼንጅ ፌስቲቫል)፣ የአፍሪካ ቀንን  ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ የሙዚቃ ፌስቲቫል ሲሆን፣ ከወራት በፊት በግዮን ሆቴል ሲካሄድ ከተለያዩ የአፍሪካ አገሮች የተውጣጡ ድምፃውያንን አሳትፏል፡፡ መርሐ ግብሩ በተካሄደበት ወቅት ከዘፋኞቹ ጎን ለጎን የታዳሚዎችን ቀልብ የሳቡት ባይላሞር በሚባል የዳንስ ትምህርት ቤት ውስጥ ከሚያስተምሩ መምህራን ጋር ይደንሱ የነበሩ ታዳጊዎች ናቸው፡፡

ሆሎካስትን በሰባት አገር ፊልሞች

አዲስ ቪዲዮ አርት ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ አገሮች የተውጣጡ የቪዲዮ ሥነ ጥበብ ውጤቶች የተካተቱበት ፌስቲቫል ሲሆን፣ በቅርቡ የፌስቲቫሉ ሁለተኛ ዙር ተካሂዷል፡፡ በአየር ንብረት ለውጥ፣ በስደትና በሌሎችም ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያጠነጥኑ የቪዲዮ ሥነ ጥበብ ውጤቶችም ቀርበዋል፡፡ ከነዚህ ሥራዎች መካከል፣ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የናዚ ጀርመኑ አዶልፍ ሒትለር ወደ ስድስት ሚሊዮን አይሁዳውያንን ያስጨፈጨፈበትን ሆሎካስት በመባል የሚታወቀውን ወቅት የተመረኮዙ የቪዲዮ ሥራ ጥበቦች ይገኙበታል፡፡

የዘጋቢ ሲዲ ምርቃት

የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ምሥረታን ጨምሮ ኢትዮጵያ ላይ ባተኮሩ የጥናትና ምርምር ውጤቶቻቸው የሚታወቁት የፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስትን የሕይወት ታሪክና ሙያዊ አበርክቶ የያዘ የ68 ደቂቃ ኦዲዮ ሲዲ ይመረቃል፡፡

የኢትዮጵያና የኢራን የባህል ልውውጥ

የኢትዮጵያና የኢራን ደራስያን የባህል ልውውጥ በሚደረግበት ዕለት፣ ኢትዮጵያውያን ገጣሚዎች በመሶብ የባህል ቡድን ታጅበው ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡ የኢራን ታዋቂ ገጣሚዎች ሥራዎች በአማርኛ ተተርጉመው ይቀርባሉ፡፡ የኢራን የባህል ቡድን አባላትም የባህል ትርኢት ያቀርባሉ፡፡

ዐውደ ርዕይ

ባለፈው ሳምንት የተከፈተው ‹‹ፍሎቲንግ ሲቲስ፤ ዲታችድ ፐርሰፕሽንስ›› የተሰኘው የአዲስ ገዛኸኝ የሥዕል ዐውደ ርዕይ በመታየት ላይ ይገኛል፡፡