Skip to main content
x

የዩኔስኮን ግብረ መልስ የሚጠብቀው የአክሱም ቅርሶች ጥገና

በካቦ የታሰረው የአክሱም ሐውልትን ጨምሮ በተለያዩ ቅርሶች ላይ የተደረገው ጥናት መጠናቀቁና ጥገና ለማከናወን የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ግብረ መልስ እየተጠበቀ መሆኑን የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን (ቅጥጥባ) አስታውቋል፡፡

ዓለም ዋንጫን በኪነ ጥበብ

ምድረ ዓለም ወሩን ሙሉ በሩሲያው የዓለም ዋንጫ ላይ እያደረገ ነው፡፡ እንደ ወትሮው ሁሉ የዜና ማሠራጫዎች ትኩረታቸውን በየአራት ዓመቱ በሚመጣው የፊፋ ዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ላይ በማድረግ ከቀጥታ ሥርጭት እስከ ክንውኑ እየዘገቡት ነው፡፡

እስላማዊ አልባሳት

በእስልምናና በዓረብኛ ሙዚቃ መካከል የተለየ ግንኙነት ባይኖርም የሙስሊም በዓላት በመጡ ቁጥር ከነሺዳና ከመንዙማው ጎን የዓረብኛ ሙዚቃዎች መክፈት የተለመደ ነው፡፡ በዓሉን አስታከው የሚካሄዱ ፕሮግራሞችና የንግድ ዝግጅቶች ማስታወቂያዎች ሳይቀሩ በዓረብኛ ሙዚቃ እንዲታጀቡ ይደረጋል፡፡

የዒድ አልፈጥር ድባብ

በሕዝበ ሙስሊሙ የረመዳን ወር በዓመተ ሒጅራ ካሉት ወሮች መካከል ዘጠነኛው ሲሆን የተቀደሰ ወር የሚያሰኘው ሙሉውን የጾም ወር መሆኑ ነው፡፡ ቀጣዩ 10ኛ ወር ሸዋል በሚብትበት ዕለት የዒድ አልፈጥር በዓል ይውላል። ይህ በጨረቃ የ354 ቀን ዑደት ላይ የተመሠረተው ዓመተ ሒጅራ፣ ዘንድሮ ጾሙን ‹ረመዳን 30 ቀን 1439 ዓመተ ሒጅራ› (ሰኔ 7 ቀን 2010) ላይ አብቅቶ በማግሥቱ ‹ሸዋል 1 ቀን› (ሰኔ 8 ቀን) ኢዱ በዓለም ዙርያ በተከታዮቹ ዘንድ ተከብሯል፡፡

‹‹ፊቼ - ጫምባላላ›› የአዲስ ዘመን ብሥራት በሲዳማ

ትውፊታዊውና ኦሪታዊው መጽሐፍ ስለ ብርሃናት ተፈጥሮ ይገልጻል፡፡ ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ በሰማያት ብርሃናት ተደረጉ ይለናል፡፡ ታላቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፣ ታናሹ ብርሃን በማታ እንዲገዛ ከዋክብትንም ፈጠረ ሲል ያክልበታል፡፡ ብርሃናቱ ፀሓይና ጨረቃ ከዋክብትም የተፈጠሩት ስለ አራት ነገሮች መሆኑንም ኦሪቱ ያብራራል፡፡ ለምልክቶችና ለዘመኖች፣ ለዕለታትና ለዓመታት በማለት፡፡

ከኦዳነቤ የተወጠነው የጅማ ጉዞ

በአሁኑ ወቅት ዱከም የሚባለው አካባቢ የቀድሞ ስያሜው ኦዳነቤ ይሰኛል፡፡ በኦዳነቤ መጫና ቱለማ የተባሉ የኦሮሞ ጎሳዎች ይኖሩበት ነበር፡፡ አፍሬና ሠዴቻ በሚል ለሁለት የተከፈሉት መጫወቻ ኦዳነቤን ትተው አምቦን ተሻግሮ በሚገኘው ጌዶ አካባቢ ሰፈሩ፡፡

ታሪካዊው የኢትዮጵያ የዘመን ቆጠራ ሲፈተሽ

ክብረ ነገሥት የሚባል በ13ኛው መቶ ዘመን እንደተጻፈ/እንደተተረጐመ የሚነገር መጽሐፍ አለ፡፡ ክብረ ነገሥት በኢትዮጵያ ለ700 ዓመታት ያህል ብሔራዊ መተዳደሪያ ሆኖ ሲያገለግል የኖረ መጽሐፍ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የቤተ ሰለሞን ሥርወ መንግሥት (ሰሎሞናይክ ዳይናስቲ) ምንጭ ለመጀመሪያ ጊዜም የተገኘው በክብረ ነገሥት ውስጥ ነው፡፡

ለአምስቱ ነገሥታት ክብር የሰጠው የአሜሪካው መድረክ

በዳያስፖራ የሚኖሩ በየአገሩ የተበታተኑ ኢትዮጵያውያን ያቋቋሙት ማኅበረ ግዩራን ዘረ ኢትዮጵያ (ኢት ዘር) በእንግሊኛው ምሕፃር ሲድ/SEED (the Society of Ethiopians Established in the Diaspora) ይባላል፡፡ በአሜሪካ ከተመሠረተ ከሁለት አሠርታት በላይ ያስቆጠረው ሲድ በስደት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ያለፉትን ነገሥታት መሪዎች በማሰብና በማክበር ያለፈውን አገራዊ ታሪክ ሕያውነት ለማስቀጠል የሚሠራ ተቋም መሆኑ ይገለጻል፡፡

‹‹ዲባቶ የኦሪት እውነት››

ከዓመታት በፊት አማርኛ ሳይንሳዊ ጽንሰ ሐሳብን መግለጽ እንዲችል ያግዛል በሚል መላ አንድ ምሁር ‹‹ሰገላዊ አማርኛ›› የሚል የጥናት መጽሐፋቸውን አሳትመው ነበር፡፡ ሰገል ጥበብ፣ ሳይንስ የሚል ሐሳብን ይይዛል በሚል ሰገላዊ አማርኛን (ሳይንትፊክ አምሃሪክ) ለኅትመት አብቅተውታል፡፡

‹‹ሹቢሳ አዳ›› የከሚሴ ባህላዊ ውዝዋዜ

በደቡብ ወሎ አካባቢ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የሚገኘው ማኅበረሰብ ከዘመናዊ ጨዋታና ውዝዋዜ ይልቅ ለባህላዊ ውዝዋዜዎችና ጨዋታዎች ክብር ይሰጣል፡፡ ማኅበረሰቡ ከሚታወቅባቸው ባህላዊ ውዝዋዜዎች መካከል ሀሚሳ፣ ሹቢሳና ውዝፍ ይጠቀሳሉ፡፡ እነዚህ ባህላዊ የውዝዋዜ ዓይነቶች ማኅበረሰቡ ዘንድ የአካባቢውን ባህልና ወግ ለማስተዋወቅ ይገለገልበታል፡፡