Skip to main content
x

የተጠሪነት ወሰን ያልተበጀለት የኢትዮጵያ ስፖርት

ሕጋዊ ሰውነት ኖሯቸው በመንቀሳቀስ ላይ ከሚገኙ መንግሥታዊ ተቋማት መካከል ስፖርቱ ይጠቀሳል፡፡ ዘርፉ በተለያየ አደረጃጀት መልክ ተጉዞ አሁን የደረሰበት ደረጃ ላይ ቢገኝም፣ ቅርፅ ያለው የተጠሪነት ወሰን ሳይበጅለት አንዴ ከባህል፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ከወጣትና ከሌሎችም ለስፖርቱ ቅርበት አላቸው ተብሎ ከሚታመንባቸው ተቋማት ጋር ሲጋባና ሲፋታ ዕድሜውን መግፋቱ፣ ዘርፉ ራሱን የቻለ ተቋማዊ ቅርፅ ብቻ ሳይሆን፣ ለተጠያቂነትና ግልጽነት እንዲሁም ለውጤታማነት በሩን ዘግቶ እንዲቆይ ምክንያት መሆኑን የሚያምኑ አሉ፡፡

ብሔራዊ የዳኞች ኮሚቴ ፌዴራል ዳኛ ጌቱ ተፈራን ለአንድ ዓመት ተኩል አገደ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ብሔራዊ የዳኞች ኮሚቴ ፌዴራል ዳኛ ጌቱ ተፈራን አገደ፡፡ በፕሪሚየር ሊጉ የሁለተኛ ሳምንት ጨዋታ ፋሲል ከተማንና ሐዋሳ ከተማን በጎንደር ስታዲየም ጨዋታውን በዋና ዳኝነት የመሩት ፌዴራል ዳኛ ጌቱ ስህተት መፈጸማቸውን ያመኑ ስለመሆኑ ጭምር ብሔራዊ የዳኞች ኮሚቴ በመግለጫው አብራርቷል፡፡

ክለቦችን ለፋይናንስ ቀውስ እግር ኳሱን ለውድቀት የዳረገው የሊጎች የጨዋታ ቅርፅ

የስፖርት ታላቅነት ከሚወሳባቸው መካከል በሕዝቦች መካከል ወዳጅነትና ወንድማማችነትን ማስፈን መሆኑ በዘርፉ የቀረቡ መዛግብት ያስረዳሉ፡፡ ለዘመናትም የስፖርት መርሆዎች ከሆኑት ውስጥ ይህ ተልዕኮው ጠበኛ አገሮችን፣ ፖለቲከኞችንና ተቀናቃኝ ወገኖችን ወደ ሰላም መንገድ ወደ አብሮነት ጥርጊያ የመምራት ኃይል የተላበሰ፣ የሰው ልጆች የአብሮነት መገለጫ ስፖርት መሆኑ እንደ ማያጠያይቅም ብዙዎች የሚስማሙበት እሴት ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡

ዓምናን በመጥፎ ያሳለፈው ፕሪሚየር ሊጉ ዘንድሮ ከችግር ይላቀቅ ይሆን?

በዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ታሪክ ውስጥ በርካታ ባላንጣ ክለቦች መካከል የሚከሰቱ ብጥብጦች በየዘመናቸው የራሳቸውን መጥፎ ገጽታ ጥለው ሲያልፉ ይስተዋላል፡፡ በበርካታ ክለቦች መካከል በሚከናወኑ ጨዋታዎች የሰው ሕይወት ሲጠፋ፣ አካል ሲጎድልና ንብረት ሲወድም መመልከት ግዴታ ሊሆን የሚችልበት አጋጣሚ ሰፊ ነው፡፡

ፕሪሚየር ሊጉ በጥቅምት ይጀመራል ፌዴሬሽኑ በስፖርታዊ ጨዋነት ላይ አጠንክሮ እየሠራ መሆኑን አስታውቋል

ሦስት ነባር ቡድኖችን አውርዶ በምትካቸው አዳዲስ ቡድኖችን ያካተተው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጥቅምት 17 ቀን 2011 ዓ.ም. እንደሚጀመር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡ ከስፖርታዊ ጨዋነት ጋር ተያይዞ ከመንግሥትና ከሚመለከታቸው አካላት በመቀናጀት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆኑንም ተናግሯል፡፡

ፕሪሚየር ሊጉን የተቀላቀለው ስሑል ሽረ የገንዘብ ድጋፍ ተደረገለት

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሚጫወቱ ክለቦች ከዋንጫ ይልቅ ወደ ከፍተኛው (ሱፐር) ሊጉ ላለመውረድ የሚያደርጉት ፉክክር የብዙዎችን ቀልብ በመግዛት ይታወቃል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ከፍተኛው ሊግ በሁለት ምድብ ‹‹ሀ›› እና ‹‹ለ›› ተከፍሎ የሚከናወን የውድድር መርሐ ግብር በመሆኑና ከየምድቡ አንድ አንድ ቡድን በቀጥታ የየምድቡ ሁለተኛ ቡድኖች ደግሞ በጥሎ ማለፍ በሚያደርጉት አንድ ጨዋታ አሸናፊው ቡድን ሦስተኛ ሆኖ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ የሚያድጉት ቡድኖች የሚለዩበት ጠንካራ ፉክክር የሚስተናገድበት በመሆኑ ነው፡፡

የክለቦች ከውጤት በኋላ መንገዳገድና የመፍረስ ዕጣ

የዓለማችን ኮከብ ተጫዋች ለሆነውና ፖርቹጋላዊው የ34 ዓመት ተጫዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ፣ የጣሊያኑ ጁቪንቱስ እግር ኳስ ክለብ፣ 112 ሚሊዮን ዩሮ ሲያፈስ ትርፉና ኪሳራውን፣ ጥቅምና ጉዳቱን ከግምት ውስጥ በማስገባት የወሰደው ዕምርጃ ስለመሆኑ ነጋሪ አይሻም፡፡

ተጠያቂ የሌለበት የተደበላለቀ የውድድር መርሐ ግብር ውጤት

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፈዴሬሽን ከሚያወዳድራቸው የውድድር መርሐ ግብሮች፣ ፕሪሚየር ሊግ፣ ከፍተኛ ሊግ (ሱፐር ሊግ) እና ብሔራዊ ሊግ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ ይሁንና ውድድሮቹ ከነባራዊ እውነታ ማለትም ክለቦቹ ካላቸው አደረጃጀት እስከ በጀት አቅማቸው ያላቸው ቁመና እንዲሁም የሚያዘወትሩባቸው ስታዲየሞችና መሰል መሠረተ ልማቶች ጋር ተጣጥሞ የውድድር ፕሮግራም ስለማይወጣላቸው ጨዋታዎቹ በጭቃ ምክንያት ሲቆራረጡና ሲዛቡ ሰነባብተዋል፡፡

ደደቢት የኢትዮጵያ ክለቦች የጥሎ ማለፍ መርሐ ግብር ይለፈኝ አለ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ሁለት አሠርታትን ካስቆጠረው የፕሪሚየር ሊጉ መጀመር ማግሥት ጀምሮ በተለይ የጥሎ ማለፍ ውድድር መርሐ ግብር በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የተጠናቀቀበት ወቅት ለመኖሩ እርግጠኛ መሆን ይከብዳል፡፡ ይባስ ብሎ ጥሎ ማለፉ አሁን ላይ ‹‹የኢትዮጵያ›› የሚለውን ስም ብቻ ይዞ መርሐ ግብሩ ሲደረግ የሚስተዋለው በፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ብቻ ሆኖ ይገኛል፡፡