Skip to main content
x

የአዲስ አዳማ የፍጥነት መንገድ የታሪፍ ለውጥ ተደረገበት

ለአዲስ አዳማ የፍጥነት መንገድ ከዚህ ቀደም ይከፈል የነበረው ታሪፍ ጭማሪ ተደረገበት፡፡ የኢትዮጵያ ክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ዓርብ፣ የካቲት 8 ቀን 2011 ዓ.ም. ይፋ ካደረገው መረጃ ለመረዳት እንደተቻለው፣ ለአንድ ሙሉ ጉዞ ከአሥር እስከ 15 ብር ጭማሪ ተደርጓል፡፡

የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ አጋርነት ቦርድ 6.5 ቢሊዮን ዶላር የሚጠይቁ 17 የኃይል ማመንጫና የፍጥነት መንገዶች በአጋርነት እንዲገነቡ ወሰነ

በቅርቡ ሥራ የጀመረው የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ አጋርነት ቦርድ፣ ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚጠይቁና ከ3,000 ሜጋዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመነጩ 14 ሜጋ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ ከ1.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚወጣባቸው ሦስት የፍጥነት መንገዶች በጠቅላላው በ6.5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ አጋርነት እንዲገነቡ ወሰነ።

ፍጥነት መንገዱና የፈጠነው ጥገና

ባሳለፍነው ቅዳሜ ወደ አዳማ ተጉዤ ነበር፡፡ ጉዞዬን ያደረኩት ከቃሊቲ መናኸሪያ በአዲሱ የፍጥነት መንገድ ነበር፡፡ ከከተማ ከወጣሁ ቆየት ብያለሁ መሰለኝ የፍጥነት መንገዱ ግራ ቀኝ የማውቀው አልመስልህ አለኝ፡፡ የመንገዱ ግራና ቀኝ በቀደመው ውበት ደረጃ ላይ አልነበረም፡፡ አንድ አዲስ የተመለከትኩት የቆሻሻ ማጠራቀሚያዎች በመንገዱ ግራና ቀኝ በተወሰነ ርቀት መቀመጣቸው ነበር፡፡ ይህ መዘጋጀቱ በጣም ጥሩ ዕርምጃ ነው፡፡

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን በስድስት ወራት

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን በ2010 ግማሽ በጀት ዓመት ከ992 ሚሊዮን ብር ወጪ የጠየቁ ሥራዎችን ያከናወነ መሆኑ አስታውቋል፡፡ ባለሥልጣኑ በበጀት ዓመቱ በመጀመርያው ስድስት ወራት ሥራ ላይ እንዲውል አቅዶ የነበረው 2.3 ቢሊዮን ብር ቢሆንም፣ የተጠቀመው ገንዘብ ግን 992 ብር ብቻ ነው፡፡ ይህ የሆነው መለቀቅ ያለባቸው ክፍያዎች ስለዘገዩ በመሆኑ ክፍያዎቹ በቀጣዮቹ ሁለት ወራት ሲለቀቁ ከዕቅዱ ጋር እንደሚጣጣም ባለሥልጣኑ አስታውቋል፡፡ ይህም ሆኖ ባለፉት ስድስት ወራት 347.8 ኪሎ ሜትር የሚሆን የመንገድ ግንባታና ጥገና ማድረጉን ይገልጻል፡፡