Skip to main content
x

አቶ ጌታቸው አምባዬ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕግ አማካሪ ሆነው ተሾሙ

የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የነበሩት አቶ ጌታቸው አምባዬ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የሕግ አማካሪ ሆነው ተሾሙ፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዲሱ ካቢኔ ባለመካተታቸው ርዕሰ ጉዳይ ሆነው የቆዩት አቶ ጌታቸው፣ ከግንቦት 10 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕግ አማካሪ ሆነው መሾማቸውን ለሪፖርተር አረጋግጠዋል፡፡

ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን በጡረታ ማሰናበት እንደሚቀጥል ተገለጸ

በመንግሥት ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ለረዥም ዓመታት ያገለገሉ ባለሥልጣናትን በጡረታ ማሰናበት እንደሚቀጥል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ይኼንን ያስታወቀው፣ አምስት ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች በጡረታ መሰናበታቸውን ማክሰኞ ግንቦት 7 ቀን 2010 ዓ.ም ይፋ ሲያደርግ ነው፡፡

የብሮድካስቲንግ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ከኃላፊነታቸው ተነሱ

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለሥልጣንን ከአራት ዓመታት በላይ በዋና ዳይሬክተርነት ሲመሩ የነበሩት አቶ ዘርዓይ አስገዶም ከኃላፊነታቸው ተነሱ፡፡ አቶ ዘርዓይ በምን ምክንያት ከኃላፊነታቸው እንደተነሱ ባይታወቅም፣ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ተሹመው የነበሩት አቶ ሰለሞን ተስፋዬ፣ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሹም ሽር በማድረግ ለ43 አመራሮች ሹመት ሰጡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በ23 በፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች የሥልጣን ሹም ሹር በማድረግ አዳዲስ ሹመቶች ሰጡ፡፡ ከተሰጡት ሹመቶች መካከል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው ረዳን በማንሳት በኡጋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩትን ደግፌ ቡላ (አምባሳደር) በሚኒስትር ማዕረግ የፌዴራል የፍትሕና የሕግ ምርምርና ሥልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አድርገው ሾመዋቸዋል፡፡

የኢንቨስትመንት ኮሚሽነሩ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ተሾሙ

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን ላለፉት አምስት ዓመታት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ፍጹም አረጋ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ተደርገው ተሾሙ፡፡ አቶ ፍጹም በአዲሱ ሥልጣናቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በመሆን፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩን እንቅስቃሴዎች የመምራትና የማደራጀት ሥራዎችን የመወጣት ኃላፊነት እንደሚይዙ ለማወቅ ተችሏል፡፡

አምባሳደር ግርማ ብሩ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሰየሙ

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት አቶ ግርማ ብሩ (አምባሳደር) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሰየሙ፡፡ አቶ ግርማ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው የተሰየሙት፣ በቅርቡ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው የተሾሙትን ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤልን (ዶ/ር) ተክተው ነው፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ካቢኔ

ከሁለት ዓመታት በፊት መስከረም 24 ቀን 2008 ዓ.ም. የፀደቀው የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣ አዋጅ መግቢያ፣ የልማታዊ መንግሥት መርሆዎችን የተከተለ ጥብቅ ትስስርና ቅንጅታዊ አሠራርን መፍጠር፣ ጠንካራና ውጤታማ የአስፈጻሚ ተቋማት መዋቅርን መፍጠር፣ የተፈጥሮ ሀብቶችን በተገቢ ሁኔታ መጠቀም ለሚያስችል አደረጃጀት ትኩረት መስጠትና በውድድር ውስጥ ተፎካካሪ መሆንን ታሳቢ ያደረገ መዋቅር መመሥረት በማስፈለጉ አዋጁ መዘጋጀቱን ይገልጻል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀይ መስመሮች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ነባርና አዲስ አመራሮች ማድረግ ወይም ማለፍ የማይችሏቸውን ቀይ መስመሮች አሰመሩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ ያቀረቧቸውን የካቢኔ አባላት ማንነትና የሚሸጋሸጉ ሚኒስትሮችን ሐሙስ ሚያዝያ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ለፓርላማ ባቀረቡበት ወቅት፣ ‹‹የሚሾሙትም ሆነ ባሉበት የሚቀጥሉት እንዲገነዘቡ የምፈልገው፣ ሕዝብ ቅሬታ የሚያቀርብበት የአገልግሎት አሰጣጥ ማስተካከል ግዴታና አንደኛው ቀይ መስመር ነው፤›› ብለዋል፡፡