ኢትዮጵያውያን ከፍ ያሉበት የበርሚንግሃም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና
ኢትዮጵያ በዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሠለፈችባቸውን ወርቃማ ድሎች ያጎናጸፏት ጥቂት አትሌቶች መሆናቸው መዛግብት ያስረዳሉ፡፡ ከተመሠረተ ከሦስት አሠርታት በላይ ባስቆጠረው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና፣ ስማቸው የሚጎላው አትሌቶች ኃይሌ ገብረ ሥላሴ፣ መሠረት ደፋር፣ ገለቴ ቡርቃ እንዲሁም የአሁኖቹ ገንዘቤ ዲባባ፣ ዮሚፍ ቀጀልቻና ሳሙኤል ተፈራ ዋነኞቹ ናቸው፡፡