Skip to main content
x

የመንግሥት ባንኮች ወደ ግል እንዲዛወሩ ፖሊሲም እንዲቀየር የሚጠይቁ ሐሳቦች 

የመንግሥት የፋይናንስ ተቋማት በለውጥ ሒደት ላይ ስለመሆናቸው ከሰሞኑ የተደረጉ የአመራሮች ለውጦች ወይም ሽግሽጎች አመላካች እየሆኑ ነው፡፡ የፋይናንስ ተቋማቱ የአመራር ለውጥ በአገሪቱ ዋና ዋና የሚባሉ ባንኮች ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡

የብሔራዊ ባንክ ገዥ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፋይናንስ ጉዳዮች አማካሪ ሆኑ

ሰሞኑን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥነት የተነሱት አቶ ተክለ ወልድ አጥናፉ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፋይናንስ ጉዳዮች ኃላፊ ሆኑ፡፡ ላለፉት 13 ዓመታት በገዥነት በቆዩት አቶ ተክለ ወልድ ምትክ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) ሲሾሙ፣ አቶ በቃሉ ዘለቀ ደግሞ ምክትል ገዥ ሆነዋል፡፡ አቶ ተክለ ወልድ የተመደቡበት የፋይናንስ አማካሪነት ኃላፊነት ለመጀመርያ ጊዜ  ራሱን ችሎ መቋቋሙ ታውቋል፡፡

በውጭ ምንዛሪ አጠቃቀም ችግር ከገበያ እየወጡ ያሉ የንግድ ሰዎች የብሔራዊ ባንክ ገዥ ይድረሱልን አሉ

በውጭ ምንዛሪ እጥረትና አጠቃቀም ችግር ምክንያት ጥሬ ዕቃ ማግኘት ባለመቻላቸው ከምርት እየወጡ መሆናቸውን የሚናገሩ የፋብሪካ ባለቤቶችና መድኃኒትን የመሳሰሉ አስፈላጊ ዕቃዎች የሚያስመጡ ነጋዴዎች፣ ከገበያ እየወጡ መሆኑን በመጥቀስ አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) እንዲደርሱላቸው ጠየቁ፡፡

ለብሔራዊ ባንክ አዲስ ገዥና ምክትል ገዥ ተሾሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የብሔራዊ የፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩትን ይናገር ደሴን (ዶ/ር) የብሔራዊ ባንክ ገዥ አድርገው ሾሙ፡፡ የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ በቃሉ ዘለቀ ምክትል ገዥ ሆነው ተሹመዋል፡፡

የብሔራዊ ባንክ ገዥና የፋይናንስ ተቋማት ኃላፊዎች በአዳዲስ አመራሮች ሊተኩ ነው

የኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማትን ሪፎርም ለማድረግ እየተደረጉ ባሉ እንቅስቃሴዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ኃላፊዎች በአዳዲስ አመራሮች ሊተኩ ነው፡፡ በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ተክለ ወልድ አጥናፉ ከኃላፊነታቸው እንደሚነሱ የተረጋገጠ ሲሆን፣ አሁን ባለው መረጃ እሳቸውን ለመተካት የብሔራዊ ፕላን ኮሚሽነር ይናገር ደሴ (ዶ/ር) በዕጩነት ቀርበዋል፡፡

የንግድ ባንክና የልማት ባንክ የብድር ፖሊሲና አሠራር ለውጥ ተደረገ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የረዥምና የመካከለኛ ጊዜ የፕሮጀክት ብድሮች መስጠት በማቆም የሥራ ማስኬጃ ብድሮች ብቻ እንዲሰጥ፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደግሞ የፕሮጀክት ብድሮች እንዲሰጥ የተላለፈው ውሳኔ ታጠፈ፡፡ ውሳኔው ከሚያዝያ 10 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ ተፈጻሚ ነበር፡፡

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ ግንቦት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. ተፈርሞ በወጣው ደበዳቤ እንደተገለጸው፣ ካሁን ቀደም የነበረው ውሳኔ ቀርቶ በቀድሞ አሠራር እንዲቀጥል ተወስኗል፡፡ በዚህም መሠረት ባለሀብቶች ከሁለቱም ባንኮች የፕሮጀክት ብድር ማግኘት ይችላሉ፡፡

ለመንፈቅ የዘገየው የንብ ባንክ ቦርድ አባላት ምርጫ በብሔራዊ ባንክ ተቀባይነት አገኘ

ከግማሽ ዓመት በላይ ውሳኔ ሳያገኝ የቆየው የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የምርጫ ውጤት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መፅደቁ ተሰማ፡፡ ከሌሎች ባንኮች በተለየ መንገድ ከስድስት ወራት በፊት የተደረገው የአመራር አባላት ምርጫ ከገዥው ባንክ ምላሽ ሳይሰጥበት ቆይቶ፣ ሐሙስ፣ ግንቦት 23 ቀን 2010 ዓ.ም. እንዲፀድቅ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል፡፡

የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ ወደ ሌላ ተቋም ተዛወሩ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥና ቺፍ ኢኮኖሚስት በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት ዮሐንስ አያሌው (ዶ/ር)፣ ከኃላፊነታቸው ተነስተው ወደ ኢትዮጵያ ልማትና ምርምር ኢንስቲትዩት ተዛወሩ፡፡ ከምክትል ገዥነታቸው ተነስተው ወደ ኢንስቲትዩቱ የመዛወራቸው ዜና ያልተጠበቀ እንደነበርም ለማወቅ ተችሏል፡፡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከ20 ዓመታት በላይ ሲያገለግሉ፣ በምክትል ገዥነትና በቺፍ ኢኮኖሚስት የቆዩት ለስምንት ዓመታት ነው፡፡

የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ ከኃላፊነታቸው ተነሱ

የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥና ዋና ኢኮኖሚስት የነበሩት ዮሐንስ አያሌው (ዶ/ር) ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

ለብሔራዊ ባንክ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለሪፖርተር እንዳስታወቁት፣ ምክትል ገዥው የተነሱት ረቡዕ ግንቦት 23 ቀን 2010 ዓ.ም. ሲሆን፣ የኢትዮጵያ የልማትና ጥናት ተቋም ዋና ዳይሬክተር ሆነዋል፡፡

ምክትል ገዥው በፋይናንስ፣ በገንዘብ ፖሊሲና በኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ የ28 ዓመታት ልምድ ያላቸው ሲሆን፣ እንግሊዝ ከሚገኘው የሰሴክስ ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡

መንግሥትና የግሉ ዘርፍ እየተነጋገሩም አልተግባቡም

የአፍሪካ ልማት ባንክ በጠራውና ይበልጥ በኢትዮጵያ የግል ዘርፍ ላይ ብቻ ባተኮረው የውይይት መድረክ ወቅት፣ የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች በመንግሥት ላይ የቆዩና ነባር ቅሬታዎችን ሲያስተጋቡ፣ መንግሥት በበኩሉ የግሉ ዘርፍ በኢኮኖሚው ውስጥ የሚያደርገው ተሳትፎ ዝቅተኛ ስለሆነ ብዙ መሥራት ይጠበቅበታል ሲል ወቀሳ አቀረበ፡፡