Skip to main content
x

አገር ባለ ውለታነቷን የምታረጋገጥበት ሥርዓታችንን እንፈትሽ!

በአገራችን የተጀመረው ለውጥ ገና ከሴራና ከአሻጥር አደጋ ውስጥ ባይወጣም፣ ለውጡ በአገር ውስጥም በውጭ አገርም ቁርሾና ኩርፊያን፣ የጠላትነት ፖለቲካን እያፈረሰ፣ ዕርቅንና የፖለቲካ ድጋፍን እያበራከተ መቀጠሉ ዋናው አዝማሚያና አቅጣጫ፣ እንዲሁም ባህርይው ነው፡፡ የዴሞክራሲ ለውጡን የተጋፈጠው አደጋ ግን ቀላልና ለአፍታም ቸል የሚባል አይደለም፡፡

ችግራችንና ሕመማችን ምንድነው? መፍትሔውስ?

በውስብስብ የመንግሥት ግርሰሳ ውስጥ ያልገባ የለውጥ ብርሃን ሲፈነጥቅ ወደ ዴሞክራሲ ጉዟችን ለስላሳ የሚሆን መስሎን ተመስገን እንዳላልን፣ ዛሬ ይኼው በምዕራቡ ዓለም የዴሞክራሲ አስተሳሰቦችና ዴሞክራሲ ምን ያህል የደፋ ቀና ረዥም መሰናዶ እንደጠየቀ እንድናስታውስና መብት ተጠምተው በአፈና አገዛዞች ላይ የተነሱ የእኛ ቢጤ አገር ሕዝቦች ሲጨነግፉና ማረኝ አምባገነንት በሚያስብል የዕልቂት እሳት ውስጥ ሲገቡ እንዳየነው፣ እኛም ዕጣችን ወደዚያ ሊሆን ይሆን ብለን እንድንጠይቅ የተገደድንበት ምዕራፍ ላይ ደርሰናል፡፡

ዓብይም የአንቀጽ 34 ሥልጣን ይኑረኝ አሉ?!

ማክሰኞ ጥቅምት 6 ቀን 2011 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ አስፈጻሚው አካል ሥልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን ተዘጋጅቶ የቀረበውን ረቂቅ ሕግ (አዋጅ) እና በዚህም መሠረት የአዲሱን የካቢኔያቸውን ዕጩዎች ሹመት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀረበበት የፓርላማ ውሎ፣ አዳዲስ የመነጋገሪያ ርዕሰ ጉዳዮችን ይዞ መጥቷል፡፡

ከሕግ በላይ ሆኖ ሕግ ማስከበር ብሎ ነገር የለም

ሕዝብ ራሱ በራሱ እያስተዳደረ ነውን? መንግሥታዊ ሥልጣን ከሕዝብ ሿሚነትና ጠያቂነት ጋር ተገናኝቶአልን? ሕዝብ ተወካዮቹን (ተወካዮች የሚባሉትን) ተወካዮች ደግሞ ራሳቸው አስፈጻሚውን መቆጣጠርና መግራት የቻሉበት አስተዳደር አለን? የሚሉ ጥያቄዎችን እንኳን በግልጽ መሰማት አልፈቅድ ብሎ የኖረው የኢትዮጵያ መንግሥት አፈናና ጭቆና፣ ኢዴሞክራሲያዊነትና ኢፍትሐዊነት ያኮማተራትን ቅስምና ሐሞት የሚያነቃቃ፣ የተዳፈነ ጆሮና ልቦናን መልሶ የሚከፍት ፖለቲካ ውስጥ መግባት የጀመረው ከ2010 ዓ.ም. መጋቢት የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) አመራር በኋላ ነው፡፡

ኢትዮጵያ የመፈራረስ አደጋ የተደቀነባት አገር

"ፈንድ ፎር ፒስ" የተሰኘው ዓለም አቀፍ ተቋም ይፋ ያደረገው የመፈራረስ አደጋ የተደቀነባቸው አገሮች ሁኔታ አመላካች ዓመታዊ ሰነድ እንደሚጠቁመው፣ ኢትዮጵያ ያለፉትን ዓመታት እጅግ የከፋ የመፈራረስ አደጋ የተጋረጠባት አገር ሆና ነው የዘለቀችው፡፡

የፖሊስ ያለህ አንልም ወይ?

የ2010 ዓ.ም. መሰናበቻና የአዲሱ ዓመት መባቻ ሦስት ሳምንታት በአዲስ አበባ ከተማ ጭምር ሁከቶችና ብጥብጦች በየመንገዱና በየመንደሩ የተዘረገፉበት፣ በዚህም ምክንያት ሕይወት በሰው እጅ የጠፋበት፣ ፖሊስም እንደ ወትሮውና እንደ ልማዱ ሠልፈኛ የገደለበት፣ እዚሁ መናገሻ ከተማው ውስጥ ሰው በገዛ አገሩ በገፍና በግፍ የተሰደደበት

ሕግና ሰላም የማስከበርና ዴሞክራሲ የመገንባት አደራ ላይ ተግባብተናልን?

በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የሚመራው መንግሥት ጥላቻና በቀልን ተፀይፎ እርቅና ይቅርታን ከፍ በማድረጉ፣ እንዲሁም የዚህ አካባቢ ባለቤት እኔ ነኝ እያሉ ሌላውን ማባረር ያጠፋናል እንጂ ‹‹አያሻግረንም››፣ የሚያሻግረን በአገር ደረጃም በቀጣና ደረጃም ‹‹መደመር›› ነው