ምን የት?
‹‹ግሎባላይዜሽን››
ሰሞኑን ‹‹ ግሎባላይዜሽን›› የተሰኘና በጌዲዮን ጌታሁን (ዶ/ር) የተዘጋጀው መጽሐፍ ለኅትመት በቅቷል፡፡ መጽሐፉ ዓለም አቀፍ የንግድ፣ የኢኮኖሚ፣ የቴክኖሎጂ፣ የትምህርት፣ የሳይንስና የማኅበራዊ ኑሮን ወቅታዊ አቋም የሚያስረዳ መሆኑ በመግቢያው ተመልክቷል፡፡
‹‹ያልታሰበው የሕይወቴ ፈታኝ ጉዞ እና የኢትዮጵያ አብዮት››
የቀድሞው መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን የነበሩት ሌተና ኮሎኔል ብርሃኑ ባይህ ያዘጋጁትና የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዴሚ ያሳተመው ‹‹ያልታሰበው የሕይወቴ ፈታኝ ጉዞ እና የኢትዮጵያ አብዮት›› መጽሐፍ, ሐምሌ 15 ቀን 2013 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዴሚ ጽሕፈት ቤት ቅጥር ግቢ ይመረቃል፡፡
ለዘንድሮ የበጎ ሰው ሽልማት የዕጩዎች ቅበላ በየካቲት ወር ይከናወናል
ለአገርና ለሕዝብ አርዓያነት ያለው ታላቅ ተግባር ያከናወኑ ኢትዮጵያውያንን በየዓመቱ ዕውቅና የሚሰጠው የበጎ ሰው ሽልማት ዘንድሮ ለሚያካሄደው ስምንተኛው የበጎ ሰው ሽልማት የዕጩዎች ጥቆማ ከየካቲት 1 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ እንደሚቀበል አስታወቀ።
ዝክረ አለባቸው ተካ
ዝግጅት፡- ኮሜዲያንና የቶክ ሾው አዘጋጅ የነበረው አለባቸው ተካ ኅልፈት 13ኛ ዓመት በተለያዩ ኪነ ጥበባዊ ዝግጅቶች ይዘከራል፡፡ቀን፡- ጥር 7 ቀን 2010 ዓ.ም. ሰዓት፡- ...
‹‹ሊቪንግ ሆም››
ዝግጅት፡- የሰይፉ አበበን ሥራዎች ያካተተ የሥዕል ዐውደ ርዕይ ‹‹ሊቪንግ ሆም›› በሚል ስያሜ ይታያል፡፡
ቀን፡- ከኅዳር 7 እስከ ኅዳር 24 ቀን 2010 ዓ.ም.