Monday, March 4, 2024

Author Name

ብሩክ አብዱ

Total Articles by the Author

407 ARTICLE

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ውሳኔ አንድምታ

በአውሮፓ ኅብረት ጠያቂነት ዓርብ ታኅሳስ 8 ቀን 2014 ዓ.ም. በተከናወነው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባ ላይ፣ ኢትዮጵያን ያሳዘነና ያስቆጣ ‹‹በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ያለ አስከፊ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት›› የሚል ርዕስ የተሰጠው የውሳኔ ሐሳብ ቀርቧል፡፡

ኢዜማ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽነሮች ምልመላና ጥቆማ ሥልጣን ለፕሬዚዳንት እንዲሰጥ ጠየቀ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ፓርቲ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ለማቋቋም በተረቀቀው አዋጅ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰጠው የኮሚሽነሮች ምልመላና ጥቆማ ሥልጣን ለፕሬዚዳንት እንዲሆን ጠየቀ፡፡

የፍትሐ ብሔር ጉዳዮችን በስምምነት መፍታት የሚያስችል መመርያ ወጣ

በፍትሐ ብሔር ጉዳዮች በተከራካሪ ወገኖች መካከል የሚነሱ አለመግባባቶችን በስምምነት ለመፍታት፣ በፍርድ ቤቶች ላይ በሚኖር የመዝገቦች መደራረብ ምክንያት ዕልባት ሳያገኙ የሚቆዩ ጉዳዮችን ጊዜ ለመቀነስና ፈጣን የፍትሕ ሥርዓት ለማስፈን ያስችላል የተባለና ‹‹የፌዴራል ፍርድ ቤት መር አስማሚነት›› የሚል ስያሜ የተሰው መመርያ ወጣ፡፡

በሽብርተኝነት የተጠረጠሩ ግለሰቦች ሕንፃዎችን የተከራዩ ከቤቶች ኮርፖሬሽን ጋር ውል እየፈጸሙ መሆኑ ታወቀ

በሽብርተኝነት ከተፈረጀው የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የተጠረጠሩ ግለሰቦች ሕንፃዎች ውስጥ ተከራይተው በንግድና በሌሎች ተግባራት የተሰማሩ ሕጋዊ ተከራዮች፣ ቤቶቹን በጊዜያዊነት ከሚያስተዳድረው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ጋር ውል እንዲያስሩ እየተደረገ ነው፡፡

‹‹ኢትዮጵያ በታሪኳ የተወሳሰበ ዲፕሎማሲ ካካሄደችባቸው ዘመቻዎች ይኼኛው አንዱ ነው›› ሬድዋን ሁሴን (አምባሳደር)፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታ

በአገሪቱ የሰሜኑ ክፍል የተፈጠረውን ግጭት አስታኮ አገሮችና የተለያዩ ተቋማት ያሏቸውን ፍላጎቶች ለማስፈጸም በማሰብ፣ የተለያዩ ጫናዎችን እያደረጉ እንደሚገኙ በመጠቆም፣ የዚህ ዘመን ዲፕሎማሲ ኢትዮጵያ ከአሁን ቀደም ካስተናገደቻቸው የተወሳሰቡ ዲፕሎማሲዎች ጋር ሊስተካከል የሚችል ነው፤›› ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታ ሬድዋን ሁሴን (አምባሳደር) ተናገሩ፡፡

መንግሥት የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ውሳኔን ፖለቲካዊ ነው አለ

መንግሥት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በጄኔቫ ያሳለፈው የውሳኔ ሐሳብ፣ ፖለቲካዊና የቀደሙ ጥረቶችን ከንቱ ለማድረግ የሚደረግ ጥረት ነው ሲል አጣጣለው፡፡

‹‹ምዕራቡ ደካማ ዓብይን ነው የሚፈልገው›› አቶ ገብርኤል ንጋቱ፣ የአትላንቲክ ካውንስል ከፍተኛ ባልደረባ

አቶ ገብርኤል ንጋቱ እንደ አፍሪካ ልማት ባንክና የዓለም ባንክ የመሳሰሉ ተቋማት የሠሩና እየሠሩ የሚገኙ የተመሰከረላቸው የፖሊሲ አማካሪ ናቸው፡፡ አቶ ገብርኤል የመጀመርያ ዲግሪያቸውን ከካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ በጂኦግራፊና ፕላኒንግ፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በኢኮኖሚ ጥናት ላይ ትኩረት በማድረግ በሕዝብና ዓለም አቀፍ አስተዳደር

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በተሾሙ የዞን አመራሮች ምትክ አዳዲስ ሹመቶች ተሰጡ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልልን የመሠረቱ ስድስት ዞኖች፣ በክልል ደረጃ ሹመት ባገኙና በተሰናበቱ አመራሮች ምትክ አዳዲስ ሹመቶችን እየሰጡ ነው፡፡ በዚህም መሠረት የካፋ ዞን፣ የቤንች ሸኮ ዞን፣ እንዲሁም የዳውሮ ዞኖች በሹመት ወደ ክልል በሄዱና በተሰናበቱ አመራሮች ምትክ አዳዲስ ሹመቶችን ሰጥተዋል፡፡

የሰሜኑ ጦርነትና የከበቡት ዓለም አቀፋዊ ፍላጎቶች

የሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ጦርነት ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ አዳዲስ ክስተቶችን ሲያስተናግድ ተስተውሏል፡፡ የጦርነቱ ወደ አፋርና አማራ ክልሎች መስፋፋትን ጨምሮ፣ በጦርነቱ ውስጥ ፍላጎት ያላቸው አካላት መበራከት የግጭቱ አንድ ባህርይ ሆኖ ሰንብቷል፡፡

በጦርነቱ ሳቢያ 5.6 ሚሊዮን የአማራ ክልል ነዋሪዎች ለችግር መዳረጋቸው ተነገረ

በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል በትግራይ፣ በአማራና አፋር ክልሎች በተስፋፋው ጦርነት ሳቢያ 5.6 ሚሊዮን የአማራ ክልል ነዋሪዎች ለችግር መዳረጋቸው ተገለጸ፡፡ በአፋር ክልል ደግሞ 260 ሺሕ ሰዎች ለችግር ተጋልጠዋል ተብሏል፡፡

Popular