Wednesday, June 12, 2024
Author Template - Week PRO | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
Author Template - Week PRO | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
Author Template - Week PRO | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

Author Name

ዳዊት እንደሻው

Total Articles by the Author

156 ARTICLE

ኦነግ ጦላይ ማሠልጠኛ የገባው ጦር ያጋጠመው የምግብ መመረዝ እንዲጣራ ጠየቀ

ጦላይ ወታደራዊ ማሠልጠኛ የገባው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ያጋጠመው ጦር የምግብ መመረዝ ተጣርቶ ለሕዝብ ይፋ እንዲደረግ ኦነግ ጠየቀ፡፡ የኦነግ ጦር አባላት እሑድ ሚያዝያ 6 ቀን 2011 ዓ.ም. ማለዳ ቁርስ ላይ ሻይ ሲጠጡ በመመረዛቸው ምክንያት የሆድ ቁርጠትና ትውከት እንዳጋጠማቸው ታውቋል፡፡ በወሊሶ ከተማም ሕክምና የተደረገላቸው ሲሆን፣ ከሕመም በስተቀር ሌላ የከፋ ጉዳት አለመድረሱ ተገልጿል፡፡

ከ2.8 ሚሊዮን በላይ ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም 700 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልጋል

በግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ከ2.8 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ለማቋቋምና ለመርዳት የሚያስችል ስትራቴጂ ተነደፈ፡፡ በሦስት ዙር ተፈናቃዮችን ለማቋቋም 700 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልጋል፡፡

የኦነግ ጦር አዲስ አበባ ካለው አመራር ጋር ያለውን ግንኙነት ማቋረጡን አስታወቀ

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በምዕራብ ኦሮሚያ ሲንቀሳቀስ የቆየው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ጦር፣ አዲስ አበባ ካሉ የኦነግ አመራሮች ጋር ያለውን ግንኙነት ማቆሙንና ከፓርቲው መነጠሉን አስታወቀ፡፡

መንግሥት አሥር ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ሊገዛ ነው

በአገሪቱ ባጋጠመው ሰብዓዊ ቀውስና በሚሊዮኖች መፈናቀል ምክንያት፣ መንግሥት አንድ ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን (አሥር ሚሊዮን ኩንታል) ስንዴ ግዥ ሊያደርግ መሆኑ ታወቀ፡፡

የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ በድጋሚ ተራዘመ

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የሚመራዉ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ኮሚሽን ዛሬ መጋቢት 9 ቀን 2011 ዓ.ም. በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ መጋቢት 29 ቀን 2011 ዓ.ም. ይደረጋል ተብሎ ዕቅድ የተያዘለት አራተኛዉ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ላልተወሰነ ጊዜ እነዲራዘም ወሰነ፡፡

በአማራ ክልል የካናቢስ አምራች ኩባንያና በነዋሪዎች መካከል ተደረገ የተባለው ውይይት ወዝግብ አስነሳ

አፍሪካና ካናቢስ የተሰኘ በአገር ውስጥና በውጭ ባለሀብቶች የተቋቋመ ኩባንያ፣ በአማራ ክልል ደምበጫ ወረዳ የካናቢስ ማምረቻ ፋብሪካ ለመክፈት ከነዋሪዎች ጋር አደረገው የተባለው ውይይት ውዝግብ አስነሳ፡፡ ኩባንያው ከ2010 ዓ.ም. ጀምሮ በክልሉ ለመድኃኒትነት የሚውል የካናቢስ ማምረቻ ፋብሪካ ለመክፈት ጥያቄ ቢያቀርብም፣ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ሳይሰጠው ቆይቷል፡፡

የድሬዳዋ ከንቲባ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኢብራሂም ዑስማን ከኃላፊነታቸው ለመልቀቅ ለከተማ አስተዳደሩ ያቀረቡት ጥያቄ በምክር ቤቱ ተቀባይነት አገኘ፡፡

የኮንዶሚኒየም ቤቶችን ለማስተላለፍ የወጣው ዕጣ ተቃውሞ ቀረበበት

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ13ኛው ዙር የኮንዶሚኒየም የመኖሪያ ቤቶችን ለማስተላለፍ የዕጣ ሥነ ሥርዓት ካደረገ በኋላ፣ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች የተቃውሞ ሠልፎች ተደረጉ፡፡ የኦሮሚያ ክልል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ውሳኔ ተቃውሟል፡፡

ፓልም የምግብ ዘይት ወደ አገር ውስጥ የማስገባት ንግድ ላይ ምርመራ ተጀመረ

መንግሥት ከዚህ ቀደም ለጥቂት ኩባንያዎች ብቻ ተፈቅዶ ወደ አገር ውስጥ ይገባ በነበረው የፓልም የምግብ ዘይት ላይ ማጣራት ሥራ መጀመሩ ታወቀ፡፡ በተለይ ከሦስት ዓመታት ወዲህ በጣት ለሚቆጠሩ ኩባንያዎች ብቻ በተሰጠ ፈቃድ፣ የምግብ ዘይት ወደ አገር ውስጥ ገብቶ ለተጠቃሚዎች ይከፋፈል እንደነበር ይታወሳል፡፡

መንግሥት ተጨማሪ 400 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ስንዴ ግዥ ሊፈጽም ነው

በአገሪቱ ባጋጠመ የስንዴ እጥረት ምክንያት መንግሥት ተጨማሪ 400 ሺሕ ሜትሪክ ስንዴ ግዥ ሊፈጽም መሆኑ ታወቀ፡፡ ግዥውን የሚያከናውነው የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ነው፡፡

Popular