Wednesday, June 12, 2024
Author Template - Week PRO | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
Author Template - Week PRO | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
Author Template - Week PRO | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

Author Name

ዳዊት እንደሻው

Total Articles by the Author

156 ARTICLE

በአማራና በደቡብ ክልሎች መስጊድና ቤተ ክርስቲያናት ተቃጠሉ

በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በተከሰቱ ሃይማኖት ተኮር ጥቃቶች አንድ መስጊድና ሰባት ቤተ ክርስቲያናት ቃጠሎ እንደ ደረሰባቸው ታወቀ፡፡ መስጊዱና ቤተ ክርስቲያናቱ ቃጠሎ የደረሰባቸው በአማራና በደቡብ ክልሎች ነው፡፡

የሶማሌ ክልል ምክር ቤት የ12 አባላትን ያለ መከሰስ መብት አነሳ

የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ሐሙስ ጥር 30 ቀን 2011 ዓ.ም. ባደረገው መደበኛ ስብሰባ፣ የ12 የምክር ቤት አመራር አባላትን ያለ መከሰስ መብት አነሳ፡፡ ያለ መከሰስ መብታቸው ከተነሳባቸው የምክር ቤት አባላት ውስጥ፣ ስድስቱ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ምንጮች ለሪፖርተር አረጋግጠዋል፡፡

በደቡብ ጎንደር መስጊዶችን ባቃጠሉ ላይ ሕጋዊ ዕርምጃ እንዲወሰድ ተጠየቀ

በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ እሑድ ጥር 26 ቀን 2011 ዓ.ም. በሦስት መስጊዶች ላይ ቃጠሎና ንብረት የማውደም ድርጊት ከተፈጸመ በኋላ፣ በአካባቢው ለሚገኙ ወጣቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ ምክክሮች ሊደረጉ መሆኑን ተገለጸ፡፡ በአጥፊዎች ላይ ደግሞ ሕጋዊ ዕርምጃ እንዲወሰድ ተጠይቋል፡፡

ኦዴፓና ኦነግ በመሀላቸው የተፈጠሩትን ችግሮች ለመፍታት ተስማሙ

በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ለወራት ሲወዛገቡ የቆዩት የክልሉ ገዥ ፓርቲ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦዴፓ) እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)፣ የኦሮሞ አባ ገዳዎች ኅብረት ባዘጋጀው የዕርቀ ሰላም ውይይት ላይ ችግሮቻቸውን ለመፍታት ከስምምነት ደረሱ፡፡

የኢትዮ ጂቡቲ ዋና መንገድ ቢከፈትም ሥጋቶች እንዳሉ ተጠቆመ

ከቀናት በፊት በአፋር ክልል በሚገኙ ቀበሌዎች ባገረሸው ግጭት ሳቢያ የኢትዮ ጂቡቲ ዋና መንገድን ጨምሮ፣ ከክልሉ ወደ ተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚያቀኑ መንገዶች ለቀናት ተዘግተው ቢከፈቱም አሁንም ሥጋቶች እንዳሉ ታወቀ፡፡

በአገር አቀፍ የውኃ ተቋማት ቆጠራ አራት ሺሕ ሰዎች ይሳተፋሉ

በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ከአራት ሺሕ በላይ ሰዎች የሚሳተፉበት አገር አቀፍ የውኃ አቅርቦት፣ ሳኒቴሽንና ኃይጂን አጠባበቅ ተቋማት ቆጠራ ሊካሄድ ነው፡፡ ቆጠራው በዋናነት በገጠርና በከተማ የውኃ ተቋማት መሠረተ ልማቶችን ከውኃ መገኛ ቦታ እስከ ማከፋፈያ ቦኖና የቤት ለቤት መስመሮችን በማካተት የሚከናወን ሲሆን፣ በዋናነት በአገሪቱ ውስጥ ያለውን የመጠጥ ውኃ አቅርቦትና ሥርጭት፣ እንዲሁም የውኃ ተቋማትን ጥራት ለማወቅ ይረዳል ተብሏል፡፡

ሁለት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት እየሰጡ አይደለም

በመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ባጋጠሙ የፀጥታ መደፍረሶችና ግጭቶች ምክንያት የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ እስከ ጥር 1 ቀን 2011 ዓ.ም. ተዘግቶ እንዲቆይ ሲወሰን፣ በተመሳሳይ ምክንያት ትምህርት መስጠት ያልጀመረው የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የቴፒ ካምፓስ ከጥር 3 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ትምህርት እንደሚጀምር ተገለጸ፡፡

ዋና ኦዲተሩ የንግድ ባንክ ቦርድ አባልነት ሹመታቸውን አልቀበልም አሉ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቦርድ አባል እንዲሆኑ የተሾሙት ዋና ኦዲተር አቶ ገመቹ ዱቢሶ ሹመቱን እንደማይቀበሉት አስታወቀ፡፡ አቶ ገመቹ እሳቸው የሚመሩት የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ኦዲት በሚያደርገው የመንግሥት ተቋም የቦርድ አባል ሆነው መሥራት የጥቅም ግጭት እንደሚፈጥር ለሪፖርተር ገልጸው፣ በዚህም ምክንያት ሹመቱን እንደማይቀበሉት አስታውቀዋል፡፡

በአፋር ክልል በተቀሰቀሰ ግጭት አራት ሰዎች ሲገደሉ 13 መቁሰላቸው ታወቀ

በአፋር ብሔራዊ ክልል ዕንድፎ በሚባለው ልዩ ቀበሌ ውስጥ በተቀሰቀሰ ግጭት ምክንያት፣ አራት ሰዎች መገደላቸውና 13 መቁሰላቸው ታወቀ፡፡ ሰኞ ታኅሳስ 15 ቀን 2011 ዓ.ም. ሌሊት በተቀሰቀሰውና እስከ ማክሰኞ ረፋድ በዘለቀው ግጭት ሳቢያ፣ ቀበሌውን አቋርጠው ወደ ትግራይና ወደ አዲስ አበባ መንገደኞችንና ጭነት የሚያመላልሱ ተሽከርካሪዎች እስከ ታኅሳስ 16 ረፋድ ድረስ መንገድ ተዘግቶባቸው እንቅስቃሴያቸው ተገድቦ መቆየታቸውን፣ ሪፖርተር ከቀበሌው ነዋሪዎች ለመረዳት ተችሏል፡፡

በአማራ ክልል በተፈጠረው ግጭት ላይ ምክክር ተደረገ

በአማራ ክልል በተለይም በምዕራብ ጎንደር ዞን የቅማንት ብሔረሰብ በሚኖርባቸው አካባቢዎች የተከሰተውንና ከ50 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ሞትና ለበርካቶች መፈናቀልና ለንብረት ውድመት ምክንያት በሆነው ግጭት ሳቢያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተገኙበት በጎንደር ከተማ ዓርብ ታኅሳስ 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ምክክር ተካሄደ፡፡

Popular