Author Name
ሔለን ተስፋዬ
Total Articles by the Author
352 ARTICLE
የፆታ ጥቃት ሰለባዎች ለፕሬዚዳንቷ የጻፉት መልዕክቶች
ሐሳባቸውን ለማጋራት የታደሉት ጥቂት ታዳጊዎች ብቻ ናቸው፡፡ ነገር ግን የእነዚህ ጥቂት ታዳጊዎች ሐሳብ የብዙ የታፈኑ ድምፆች ወኪል ሊሆን እንደሚችል ይታመናል፡፡
የወር አበባ ንፅሕና መጠበቂያ ላይ የቀረጥና ታክስ ማሻሻያ ተደረገ
የወር አበባ ንፅህና መጠበቂያ ሞዴስና የሕፃናት ንፅህና መጠበቂያ (ዳይፐር) ላይ የቀረጥና የታክስ ማሻሻያ መደረጉን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ገቢ ምርቶች በአገር ውስጥ እንዲመረቱ ለማስቻልና የአገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች እንዲበረታቱ በመሠረታዊ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች በተለይም በወር አበባ ንፅህና መጠበቂያ ምርቶች ላይ የቀረጥና ታክስ ማሻሻያ ማድረጉን ያስታወቀው ሚኒስቴሩ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ከውጭ ሲገቡ ቀድሞ ከነበረው ከፍተኛ የታክስ ምጣኔ 30 ከመቶ ዝቅ ተደርጎ ታክሱ 10 በመቶ ብቻ እንዲሆን መወሰኑን ገልጿል፡፡
ከ1.4 ሚሊዮን በላይ የመሬት ይዞታዎችን በአምስት ዓመታት ለመመዝገብ ቢሠራም ክንውኑ 435 ሺሕ ብቻ መሆኑ ተገለጸ
ላለፉት አምስት ዓመታት ከ1.4 ሚሊዮን በላይ የመሬት ይዞታዎችን በዘመናዊ መንገድ ለመመዝገብና ለማረጋገጥ ታቅዶ ሥራ ቢጀመርም፣ 435 ሺሕ ይዞታዎች ብቻ በሥርዓቱ መካተታቸውን፣ የፌዴራል የከተማ መሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡
የከተማ ላዳ ታክሲዎች በአንድ ዓመት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ በአዲስ ይተካሉ ተባለ
በተለምዶ ሰማያዊ ላዳ ታክሲዎች የሚባሉ ተሽከርካሪዎች፣ በአንድ ዓመት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ በአዲስ እንደሚተኩ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡
የገና ባዛር በኮቪድ-19 ጥላ ሥር
አምና የገና ዋዜማን በማስመልከት በተለያዩ ቦታዎች የውጭና የአገር ውስጥ ነጋዴዎችን ያሳተፉ ባዛሮች እንደነበሩ ይታወሳል፡፡ ገና ሊደርስ ሳምንት ያህል ሲቀረው ይበልጥ ከደመቁት ባዛሮች ጥቂቶቹ በተለይም በየጎዳናው በነጭ ድንኳን የተከናወኑት እስከ ጥምቀት ዘልቀው ነበር፡፡
ሚኒስቴሩ 15 ማዕድናትና የነዳጅ ሀብት ለውጭና ለአገር ውስጥ ኢንቨስተሮች በጨረታ ሊቀርብ ነው
የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር አሥራ አምስት ማዕድናትና የነዳጅ ሀብት ለውጭና ለአገር ውስጥ ኢንቨስተሮች ለጨረታ ሊያቀርብ መሆኑን አስታወቀ፡፡
በሚኒስቴሩ ጥናት የተደረገባቸው ለአገር ውስጥ ፍጆታና ለውጭ ንግድ የሚውሉ ሲሚንቶ፣ የከሰል ድንጋይ፣ ማዳበሪያ፣ ብረት፣ ወርቅ፣ ታንታለም፣ ጀምስቶንና የነዳጅ ሀብት ለኢንቨስትመንት ክፍት መደረጋቸውን ታኅሳስ 20 ቀን 2013 ዓ.ም. ለመገናኛ ብዙኃን በተሰጠው መግለጫ ተጠቁሟል፡፡
የቀድሞውን የጉማይዴ ወረዳ ለማስመለስ በተነሳው አለመግባባት የሰብዓዊ መብት ጥሰት መድረሱ ተገለጸ
በደቡብ ክልል የቀድሞውን የጉማይዴ ወረዳ ለማስመለስ በተደረገ እንቅስቃሴ ምክንያት በተነሳው አለመግባባት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየደረሱ መሆኑን፣ 145 ሺሕ ወክለው ወደ አዲስ አበባ የመጡት የጉማይዴ ሕዝብ የሰላም ኮሚቴ አባላት አስታወቁ፡፡
ዳግም ያሠጋው የአንበጣ መንጋ
አርሶ አደሩ የዕለት ጉርሱን የሚያገኝበትን ማሳ መና አስቀርቷል፡፡ ለሚበሉት የተቸገሩም አሉ፡፡ ያለ አባ ወራ ልጆቻቸውን በግብርና የሚያስተዳድሩ እንስቶችንም ተስፋ አስቆርጧል፡፡
የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው መመርያ እንዲተገበር ዳግም ጥሪ ቀረበ
በኅብረተሰቡ እየተዘነጋ ያለው የኮሮና ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው መመርያ እንዲተገበር ጤና ሚኒስቴር ዳግም ጥሪ አቅርቧል፡፡
በአሥር ክፍሎች የቀረበው መመርያ በዋናነት በሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች፣ የመንግሥትና የግል ሴክተሮች ያለው መዘናጋት እንዳይኖር የሚመራ ሲሆን፣ ኅብረተሰቡ ወደ ነበረበት የጥንቃቄ ዕርምጃ እንዲመለስ የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) ማክሰኞ ታኅሣሥ 13 ቀን 2013 ዓ.ም. ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የበይነ መረብ ልመና
እንደተለመደው የገጽ ለገጽ ልመና ወይም በአካል ቦታው ተገኝቶ መለመን የማይጠበቅበት የልመና ዓይነት ብቅ ማለት ከጀመረ ሰንብቷል፡፡ በማኅበራዊ ትስስር ገጽ በሚደረግ ልመናና በሚቀመጥ የባንክ ደብተር ቁጥር ብዙዎች ተረድተው ብሎም ከችግራቸው ወጥተው ሊሆን ይችላል፡፡