Wednesday, February 28, 2024

Author Name

ምሕረተሥላሴ መኰንን

Total Articles by the Author

367 ARTICLE

ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በተለያዩ ወንጀሎች የተመዘበረ ከ2.1 ቢሊዮን ብር በላይ ሀብት ማስመለሱን አስታወቀ

ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በ2013 በጀት ዓመት በዓይነት ገቢ የተደረጉ ንብረቶችን ጨምሮ፣ በሙስናና በሌሎች የተደራጁ የኢኮኖሚ ወንጀሎች የተመዘበረ 2,162,175,071 ብር የሚገመት ሀብት ማስመለስ መቻሉን አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያና የኢራን ጥበባዊ ትስስር

የምሽቱ መርሐ ግብር የተጀመረው በመሶብ ባንድ ባህላዊ ሙዚቃዎች ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የተገኙትን ታዳሚዎች በሙዚቃዎቻቸው ዘና አድርገዋል፡፡ ባንዱ በተለይም ግጥም በጃዝ በሚቀርብባቸው የሥነ ጽሑፍ ምሽቶች በባህላዊ ሙዚቃ የግጥም ሥራዎችን በማጀብ ይታወቃል፡፡ በክራር፣ በመሰንቆ፣ በዋሽንትና በከበሮ ውህድ ግጥሞቻቸውን ያስደመጡ ጸሐፍትም በርካታ ናቸው፡፡

የሳልሳ ሀሁ…

የአፍሪካ ሙዚቃና ባህል ልውውጥ ፌስቲቫል (አፍሪካ ሚውዚክ ኤንድ ካልቸራል ኤክስቼንጅ ፌስቲቫል)፣ የአፍሪካ ቀንን  ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ የሙዚቃ ፌስቲቫል ሲሆን፣ ከወራት በፊት በግዮን ሆቴል ሲካሄድ ከተለያዩ የአፍሪካ አገሮች የተውጣጡ ድምፃውያንን አሳትፏል፡፡ መርሐ ግብሩ በተካሄደበት ወቅት ከዘፋኞቹ ጎን ለጎን የታዳሚዎችን ቀልብ የሳቡት ባይላሞር በሚባል የዳንስ ትምህርት ቤት ውስጥ ከሚያስተምሩ መምህራን ጋር ይደንሱ የነበሩ ታዳጊዎች ናቸው፡፡

ሆሎካስትን በሰባት አገር ፊልሞች

አዲስ ቪዲዮ አርት ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ አገሮች የተውጣጡ የቪዲዮ ሥነ ጥበብ ውጤቶች የተካተቱበት ፌስቲቫል ሲሆን፣ በቅርቡ የፌስቲቫሉ ሁለተኛ ዙር ተካሂዷል፡፡ በአየር ንብረት ለውጥ፣ በስደትና በሌሎችም ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያጠነጥኑ የቪዲዮ ሥነ ጥበብ ውጤቶችም ቀርበዋል፡፡ ከነዚህ ሥራዎች መካከል፣ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የናዚ ጀርመኑ አዶልፍ ሒትለር ወደ ስድስት ሚሊዮን አይሁዳውያንን ያስጨፈጨፈበትን ሆሎካስት በመባል የሚታወቀውን ወቅት የተመረኮዙ የቪዲዮ ሥራ ጥበቦች ይገኙበታል፡፡

የሥነ ጽሑፍ ምሽቶች አበርክቶ

የሥነ ጽሑፍ ወዳጆች፣ ስለ ሥነ ጽሑፍ መርሐ ግብሮች ሲያስቡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ማስታወሳቸው አይቀርም፡፡ የሥነ ጽሑፍ ትምህርት ክፍል መገኛ የሆነው ዩኒቨርሲቲው ውስጥ ባለው የባህል ማዕከል በርካታ የሥነ ጽሑፍ ምሽቶች ተካሂደዋል፡፡ የበርካታ አንጋፋ ጸሐፍት መነሻም ማዕከሉ ነው፡፡ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ተማሪዎች ባሻገር የሌሎች ትምህርት ክፍሎች ተማሪዎችም የሥነ ጽሑፍ ምሽቶቹን በጉጉት ይጠባበቃሉ፡፡ ምሽቶቹ በርካታ የሥነ ጽሑፍ ውጤቶች የቀረቡባቸው እንዲሁም ዛሬ ላይ በሥነ ጽሑፍ ስመጥር የሆኑ ባለሙያዎች የወጡባቸውም ናቸው፡፡ እንደ ምሳሌ በዕውቀቱ ሥዩምን ማንሳት ይቻላል፡፡

የወርቅ ኢዮቤልዩ ላይ የደረሰው የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት

ያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት የተመሠረተው በ1960 ዓ.ም. ሲሆን፣ 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩውን ከጥር 3 ቀን እስከ ጥር 5 ቀን 2010 ዓ.ም. አክብሯል፡፡ በክብረ በዓሉ ትምህርት ቤቱ በሙዚቃ ዘርፍ ስላበረከተው አስተዋፅኦ፣ ስለገጠሙት ተግዳሮቶችና የወደፊት እቅዶቹ ውይይት ተደርጓል፡፡ በትምህርት ቤቱ የ50 ዓመት ጉዞ ዙሪያ የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ኃላፊና የቫዮሊን መምህርት ሰላማዊት አራጋውን ምሕረተሥላሴ መኰንን አነጋግራታለች፡፡

ሙዚቃ ለሰላም

‹‹ሚውዚክ ፎር ፒስ›› (ሙዚቃ ለሰላም) የተሰኘ የሙዚቃ ኮንሰርት የተካሄደው የአፍሪካን አርቲስትስ ፒስ ኢንሽዬቲቭ (ኤኤፒአይ) ፎረምን ተከትሎ ነበር፡፡ በአፍሪካ ውስጥ ያሉ አርቲስቶችና የመብት ተሟጋቾች ስብስብ የሆነው ኤኤፒአይ፣ የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤን አስታኮ የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር፡፡ የውይይቱ ቀዳሚ ትኩረት ሙስናን በመዋጋት ረገድ አፍሪካውያን አርቲስቶች ምን ሚና አላቸው? የሚለው ነበር፡፡ በውይይቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ የአፍሪካ አገሮች የተውጣጡ ድምፃውያን፣ ገጣሚዎች፣ ዲዛይነሮች፣ ፊልም ሠሪዎችና ሌሎችም የጥበብ ሰዎች ተሳትፈዋል፡፡ ጥር 16 ቀን 2010 ዓ.ም. የተጀመረው ውይይት የተገባደደው ጥር 19 በተካሄደው የሙዚቃ ኮንሰርት ነው፡፡

ሙስናን በጥበብ መዋጋት

ፒላቶ በሚል የመድረክ ስሙ የሚታወቀው ዛምቢያዊው አቀንቃኝ ፉምባ ቻማ የዛምቢያውን ፕሬዚዳንት ኤድጋር ሉንጉና የፖለቲካ ፓርቲያቸውን የሚተች ‹‹ኮስዌ ሙምፓቶ›› የተሰኘ ዘፈን የለቀቀው በቅርቡ ነበር፡፡ ‹‹በማሰሮ ውስጥ ያለ አይጥ›› የሚል ትርጓሜ ያለው ዘፈኑ እንደተለቀቀ በመላው አገሪቱ ይደመጥ ጀመር፡፡ በዘፈኑ፣ የአገሪቱ ፖለቲከኞች እንደ አይጥ ምግብ ብቻ ሳይሆን የማይጠቅሙ ነገሮችንም ከሕዝቡ እየሰረቁ መሆኑን ይገልጻል፡፡ ዘፈኑ በሬዲዮና ቴሌቭዥን ከመቅረቡ ባሻገር ፒላቶ በተለያዩ መድረኮች እንዲያቀነቅነው ተጠይቋል፡፡ ነገሩ ያልተዋጠላቸው የአገሪቱ አመራሮች ዘፈኑ በመገናኛ ብዙኃን እንዳይሰራጭና ፒላቶም ኮንሰርቶቹን እንዲሰርዝ ትዕዛዝ አስተላለፉ፡፡

እውንነት አስመሳዩ ጥበብ

በጎተ ኢንስቲትዩት አዳራሽ ውስጥ በተሽከርካሪ ወንበር የተቀመጡ ወጣቶች ይታያሉ፡፡ ሁሉም ጆሯቸው ላይ ሔድፎን፣ ዓይናቸው ላይ የቨርችዋል ሪያሊቲ መነፅር አድርገዋል፡፡ በመነፅሩ የሚመለከቱት ፊልም የፈጠረባቸውን ስሜት ከሰውነታቸው እንቅስቃሴ መረዳት ይቻላል፡፡ በፊልሙ አስጨናቂ ነገር ሲያዩ በእውን የሆነ ያህል ስለሚሰማቸው መነፅሩን ለማውለቅ ይቃጣቸዋል፡፡ በፊልሙ አስገራሚ ትዕይንት ሲመለከቱ፣ የሚያዩትን ለማጣጣም ወንበሩን በተለያየ አቅጣጫ ያሽከረክራሉ፡፡

‹‹በዕድሜ ጎዳና ላይ የጉዞ ትዝታ››

ማዕከላዊ እስር ቤት ተዘግቶ ወደ ሙዚየምነት እንደሚለውጥ በተገለጸ በጥቂት ቀናት ለንባብ የበቃው የ100 ዓመት ዕድሜ ባለፀጋው በለጠ ገብሬ መጽሐፍ፣ የጸሐፊውን የማዕከላዊ ትውስታ ያትታል፡፡ በእስር ቤቱ ስለደረሰባቸው እንግልትና በወቅቱ አብረዋቸው ታሰረው ከነበሩ ሰዎች ጋር ስለነበራቸው ታሪክም የሚዳስስ መጽሐፍ ለንባብ አብቅተዋል፡፡ ጥር 3 ቀን 2010 ዓ.ም.  ‹‹በዕድሜ ጎዳና ላይ የጉዞ ትዝታ›› በሚል የተመረቀው ሁለተኛው መጽሐፍ የማዕከላዊ የእስራት ዘመናቸው ምን ይመስል እንደነበር ያሳያል፡፡

Popular