Tuesday, February 27, 2024

Author Name

ሰለሞን ጐሹ

Total Articles by the Author

147 ARTICLE

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ያልተለመዱ ግምገማዎችና ውሳኔዎች ተግባራዊነት በጉጉት እየተጠበቀ ነው

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለ17 ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን ዝግ ስብሰባ አጠናቆ በመጨረሻ ባወጣው መግለጫና አራቱ የኢሕአዴግ አባል ድርጀቶች ሊቃነ መናብርት ታኅሳስ 25 ቀን 2010 ዓ.ም. በጋራ በሰጡት መግለጫ፣ በእስር ላይ የሚገኙ ፖለቲከኞችና ሌሎች ግለሰቦች እንደሚፈቱና ‹‹ማዕከላዊ›› በመባል የሚታወቀው የምርመራ ማዕከል እንደሚዘጋ ማስታወቃቸውን ጨምሮ ‹‹ያልተለመዱ›› የተባሉት ግምገማዎችና ውሳኔዎች ተግባራዊነት በጉጉት እየተጠበቀ ነው፡፡

‹‹ኢሕአዴግ ካለፈው አስከፊ ሥርዓት ቢያላቅቀንም የራሱን አዲስ ቀንበር ግን ጭኖብናል›› ዳኛቸው አሰፋ (ዶ/ር)፣ የፍልስፍና መምህርና ተንታኝ

ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ለረዥም ዓመታት ፍልስፍናን አስተምረዋል፡፡ ለሦስት አሥርት ዓመታት ገደማ ከኖሩበት አሜሪካ መጥተው ኢትዮጵያ መኖር ከጀመሩ ዘጠኝ ዓመታት አልፏቸዋል፡፡ በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ትንታኔ በመስጠትም ይታወቃሉ፡፡ ሰለሞን ጎሹ አበክረው በሚጽፉባቸው ርዕሶችና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አነጋግሯቸዋል፡፡

የደቡብ ሱዳን አዲሱ የተኩስ አቁም ስምምነትና የተደቀነው ሥጋት

የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ የፖለቲካ ኃይሎች ወደ እርስ በርስ ጦርነት ካመሩ አራት ዓመታት አለፉ፡፡ ይህ ግጭት ቆሞ በአገሪቱ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ለማድረግ የተለያዩ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡ በተለይ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግሥታት (ኢጋድ) ሁለቱ ኃይሎች ያነገቡትን መሣሪያ በመጣል፣ ወደ ጠረጴዛ ውይይት እንዲመጡ ተደጋጋሚ ጥረት በማድረግ ተጠቃሽ ነው፡፡

‹‹የሕገ መንግሥት ‘ሪፎርም’ ለብዙ ዘመናት ሲንከባለሉ ለመጡና ለሚጨመሩ አንገብጋቢ አገራዊ ችግሮቻችን መላ የምንፈልግበት ዕድል ይሰጠናል››

አቶ ሞላ ዘገዬ፣ የሕግ አማካሪና ጠበቃ አቶ ሞላ ዘገዬ ጠበቃና የሕግ አማካሪ ናቸው፡፡ አቶ ሞላ ከንጉሠ ነገሥቱ ዘመን ጀምሮ በውትድርና፣ በፖለቲካና አስተዳደር የመንግሥት ሥራ ያገለገሉም ናቸው፡፡ በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ትንታኔ በመስጠትም ይታወቃሉ፡፡ የ‘ውይይት’ መጽሔት ማኔጂንግ ኤዲተርም ናቸው፡፡ በቅርቡም በሕገ መንግሥት ‘ሪፎርም’ ላይ አነስ ያለ መጽሐፍ አሳትመዋል፡፡

‹‹የግብፅን የዓባይ የውኃ ድርሻ ማንም እንደማይነካው ለግብፃዊያን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ›› አብዱልፈታህ አልሲሲ፣ የግብፅ ፕሬዚዳንት

በህዳሴ ግድቡ ላይ ስምምነት መፍጠር እንዳልተቻለ ግብፅ ለአሜሪካ ማሳወቋ ተጠቁሟል የግብፅን የዓባይ የውኃ ‹‹ለአገሪቱ የሞትና የሽረት ጉዳይ ነው›› ያሉት የግብፅ ፕሬዚዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ በመካከለኛው ምሥራቅ ትልቁ ነው የተባለው የዓሳ ማምረቻ ከቀናት በፊት በተመረቀበትና በቴሌቪዥን በተላለፈ ንግግራቸው፣ ‹‹የግብፅን የዓባይ የውኃ ድርሻ ማንም እንደማይነካው ለግብፃዊያን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፤›› ብለዋል፡፡

ሕገ መንግሥታዊነትን የማረጋገጥ ጫናና ዝግጁነት

የ1987 ዓ.ም. የኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት ሥራ ላይ ከዋለ 22 ዓመታት አለፉ፡፡ ሕገ መንግሥቱ ከመሠረታዊ መብቶች ጋር ስምሙ የሆነ የሕግና የፖለቲካ ሰነድ እንደሆነ ብዙዎች ቢስማሙም፣ በተግባር ላይ ስለመዋሉ ወይም ሕገ መንግሥታዊነቱ ስለመረጋገጡ፣ ወይም ለሰብዓዊ መብት መረጋገጥ ዋስትና የመሆኑ ጉዳይ ግን አወዛጋቢ ሆኖ ቀጥሏል፡፡

‹‹በእኔ ዕይታ የአፈጻጸም ክፍተት ካልሆነ በስተቀር የፌዴራል ሥርዓቱ ችግር አላመጣም››

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ የኢፌዴሪ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ከ1987 ዓ.ም. እስከ 1993 ዓ.ም. የኢፌዴሪ ርዕሰ ብሔር ወይም ፕሬዚዳንት ነበሩ፡፡ ከዚያ በፊት በሽግግሩ ጊዜ በመጀመርያ የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር፣ በኋላ የማስታወቂያ ሚኒስትር፣ እንዲሁም ጎን ለጎን የፓርላማ አባል ነበሩ፡፡ ከ1984 ዓ.ም. እስከ 1987 ዓ.ም. ሥራ ላይ የነበረውና የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥትን ያረቀቀው የሕገ መንግሥት አርቃቂ ኮሚሽንም አባል ነበሩ፡፡ ሕገ መንግሥቱን ያፀደቀው የሕገ መንግሥት ጉባዔም አባልና ሰብሳቢ ነበሩ፡፡

የታላቁ ህዳሴ ግድብ አካባቢያዊ ፋይዳ

በኢትዮጵያ፣ በግብፅና በሱዳን መካከል ያለው ግንኙነት ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ግንባታን የመሠረት ድንጋይ መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም. ከጣለች በኋላ ይበልጥ ተወሳስቦ ነበር፡፡ ግድቡ በሁለቱ አገሮች ላይ መሠረታዊ ጉዳት ያስከትላል? አያስከትልም? የሚለው ጉዳይ አዲስ የውዝግብ አጀንዳ ሆኖ ነበር፡፡ መጀመርያ ላይ ሁለቱም ግድቡን ተቃውመው እንዲቆም ጠይቀው ነበር፡፡

የፌዴራል መንግሥቱ ፈተናዎች

‹‹እኛ አጥብበን በመንደር ታጥረን የምናስብ ሰዎች አይደለንም፡፡ ለመላው የአገራችን ሕዝቦች ብልጽግናና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት የምናስብ ሰዎች ነን፡፡ የአገራችንን ዕድገት ለማፋጠን የእኛ ሚና ወሳኝ እንደሆነ በአግባቡ እንገነዘባለን፡፡ ከጥልቅ ተሃድሶው መጀመር ወዲህ ከመሬት፣ ከማዕድን፣ ከኮንትሮባንድና ከመሳሰሉት ጉዳዮች ጋር ተያይዘው በሚስተዋሉ የኪራይ ሰብሳቢነት ተግባራት ላይ ዕርምጃ መውሰድ ጀምረናል፡፡

ተቃዋሚዎች ገሸሽ የሚያደርጉት ኢሕአዴግ ብቻውን የሚያሸንፍበት አካባቢያዊ ምርጫ

አገሪቱን ባለፉት ሦስት ዓመታት ከገጠማት የፖለቲካ ቀውስና አለመረጋጋት ለማውጣት መንግሥት የተለያዩ ዕርምጃዎች እየወሰደ ቢሆንም፣ ችግሮቹ መልካቸውን እየቀያየሩ የቀጠሉ ይመስላል፡፡ የ‘ጥልቅ ተሃድሶ’ የፓርቲና የመንግሥት ግምገማ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ አስተዳደራዊ ዕርምጃዎችና የፀረ ሙስና ዘመቻዎች አገሪቱን ወደ ነበረችበት መረጋጋት መልሰዋታል ለማለት አዳጋች ነው፡፡

Popular