Sunday, April 14, 2024

Author Name

ሰለሞን ጐሹ

Total Articles by the Author

147 ARTICLE

‹‹በአገሪቱ አካባቢያዊ ዴሞክራሲ ለማስፈን የአካባቢያዊ አስተዳደሮችን ሥልጣንና ተግባር በግልጽ ማስቀመጥ የግድ ይላል››

ዶ/ር ዘመላክ ዓይነተው፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፌዴራሊዝም ጥናት ማዕከል መምህር ዶ/ር ዘመላክ ዓይተነው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፌዴራሊዝም ጥናት ማዕከል ተባባሪ ፕሮፌሰር ሲሆኑ፣ በዌስተርን ኬፕ ዩኒቨርሲቲ ዱላህ ኦማር ኢንስቲትዩት ኤክስትራኦርዲናሪ ተባባሪ ፕሮፌሰር ናቸው፡፡ ዶ/ር ዘመላክ በአካባቢያዊ አስተዳደር ላይ ትኩረት ያደረጉ የሕገ መንግሥት ኤክስፐርት ናቸው::

በመንግሥት አሠራር ላይ ጉልህ ተፅዕኖ ማሳደር የተሳነው ሚዲያ

በተጠናቀቀው ዓመት መንግሥት በተወሰኑ በኃላፊነት ደረጃ በሚሠሩ የመንግሥት ሠራተኞችና የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት ላይ የጀመረው የሙስና ምርመራን ጨምሮ፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በመንግሥት መዋቅርና አሠራር ላይ ጉልህ ክፍተት ስለመኖሩ በርካታ መረጃና ማስረጃ ማቅረብ ይቻላል፡፡

የለውጥ ያለህ የሚለው የግሉ ሚዲያ

በተለያዩ ማኅበራዊ ድረ ገጾች ላይ ኢትዮጵያ በሚኖሩ ዜጎች ወይም ውጭ አገር በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መካከል የሚደረጉ የሐሳብ ልውውጦችን የተመለከተ ሰው፣ የአገሪቱ ዜጎች የፖለቲካ አመለካከት በተለያየ ጽንፍ ላይ እንደሚገኝ ይገነዘባል፡፡

ኢትዮጵያና ግብፅ በዳግም ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት

የኢትዮጵያ፣ የግብፅና የሱዳን ግንኙነት በማንኛውም መሥፈርት እጅግ የተወሳሰበ ነው፡፡ ለዘመናት በእርስ በርስ ጦርነት፣ ግጭትና ፖለቲካ ፍትጊያ ውስጥ አልፈዋል፡፡ አልፎ አልፎም ሁለት ሆነው በማበር አንዱ ላይ ጥቃት ለመፈጸም ያሴሩበት አጋጣሚም ነበር፡፡

‹‹የስደትን አደጋ ለመቀነስና ጥቅሙንም ለማስፋት የፖለቲካውን አጥር እንደምንም አስወግዶ መነጋገር ያስፈልጋል››

አቶ ዮርዳኖስ አልማዝ ሰይፉ በጂማ ዩኒቨርሲቲ የመጀመርያ ዲግሪያቸውን በምጣኔ ሀብት (ኢኮኖሚክስ) ዘርፍ ይዘዋል፡፡ ከዚያ በኋላ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዲግሪያቸውን በሥነ ሕዝብ፣ እንዲሁም ጀርመን በሚገኘው ኦልድንበርግ ዩኒቨርሲቲ ሌላ ሁለተኛ ዲግሪ በስደትና የባህል ግንኙነት (Migration and Intercultural Relations) ላይ ወስደዋል፡፡

የሕገ መንግሥቱ ቅቡልነትና ተፈጻሚነት አሁንም እያከራከረ ነው

ባለፉት 23 ዓመታት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሚዲያዎች፣ ሲቪል ማኅበራት፣ ሙያ ማኅበራትና ምሁራን በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት ላይ ጥያቄዎች ማንሳታቸውና አሉታዊ ትንታኔዎች መስጠታቸው የተለመደ ነበር፡፡

‹‹አንዳንድ የባንክ አሠራሮች ግልጽ ከሆነው ሕግ በማፈንገጥ በልማድ የዳበሩ ናቸው››

አቶ ገዙ አየለ መንግሥቱ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሕግ ባለሙያነት በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡ አቶ ገዙ በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን (LL.B) ከጅማ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም የሁለተኛ ዲግሪያቸውን በዚያው በሕግ ሙያ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል። በሥራ መስክም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት፣ በሕግ መምህርነትና በተመራማሪነት ከአምስት ዓመታት በላይ አገልግለዋል። በዩኒቨርሲቲው ቆይታቸውም የተለያዩ የምርምር ሥራዎችን አበርክተዋል።

የፖለቲካ ሹማምንት ዲፕሎማትነት መበራከትና አንድምታው

ከቀናት በፊት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) ኢትዮጵያን በውጭ አገር ለሚወክሉ አምባሳደሮች ሹመት ሰጥተዋል። በዚህም መሠረት በባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት የተሾሙት አቶ ካሳ ተክለ ብርሃን፣ ወ/ሮ አስቴር ማሞ፣ ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም፣ አምባሳደር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ፣ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና፣ አቶ ዓሊ ሱሌይማን፣ ፕሮፌሰር አድማሱ ፀጋዬ፣ አምባሳደር ተበጀ በርሄ፣ አቶ መታሰቢያ ታደሰ፣ አቶ ሙሉጌታ ዘውዴና ወ/ሮ ሉሊት ዘውዴ ናቸው፡፡

‹‹የመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊዎች ብለን የምናስባቸው በሚኒስትር ማዕረግ ያሉትን ከሆነ ስህተት ነው››

የመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊዎች የሚባሉት በሚኒስትርና በሚኒስቴር ዴኤታ ማዕረግ ብቻ ያሉት አለመሆናቸውን፣ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አቶ ጌታቸው አምባዬ አስታወቁ፡፡ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ ይህንን ያሉት ቅዳሜ ሐምሌ 22 ቀን 2009 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና የሥራ ቀጣሪዎች ትስስር ገፊዎች

በአዲስ አበባ ከተማ ሁሌም በሰዎች ከሚጨናነቁ ቦታዎች መካከል አራት ኪሎ ጆሊ ባር አጠገብ የሥራ ማስታወቂያ የሚለጠፍባቸው ሰሌዳዎች የሚገኙበት ቦታ ተጠቃሽ ነው፡፡ በዚህ ሥፍራ በአብዛኛው አዳዲስ የዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች የሚታዩ ቢሆንም፣ እንደ ቅዱስ ሥፍራ ለዓመታት የተመላለሱበትን ወጣቶች ማግኘት ብርቅ አይደለም፡፡

Popular