Thursday, September 21, 2023

Author Name

ውድነህ ዘነበ

Total Articles by the Author

903 ARTICLE

የከተማ አስተዳደሩ ከአሥር ቢሊዮን ብር በላይ የሚወጣባቸው ፕሮጀክቶችን ለውጭ ኮንትራክተሮች ሰጠ

በምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) የሚመራው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥልጣን በተረከበ አንደኛ ዓመት ማግሥት፣ በከተማው ገጽታ ላይ መሠረታዊ ለውጥ ያመጣሉ የተባሉ ስድስት ፕሮጀክቶችን ለውጭ ኩባንያዎች ሰጠ፡፡

በአካባቢ ተቆርቋሪዎችና በኢንዱስትሪ አቀንቃኞች መካከል አለመግባባት በመፈጠሩ የሶዳ አሽ ፋብሪካ ሥራ አቆመ

በአብያታና በሻላ ሐይቆች በሚካሄድ ልማት በአካባቢ ተቆርቋሪዎችና በኢንዱስትሪ አቀንቃኞች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ሥራ በመስተጓጎሉ፣  ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መመርያ እንዲሰጡ ተጠየቀ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከ11 ቢሊዮን ብር በላይ የወጣበትን የያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ እንዲታደጉ ተጠየቀ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ጣልቃ ገብተው እንዳስተካከሉት ሁሉ፣ ትልቅ ተስፋ ቢጣልበትም በአሁኑ ወቅት እየመከነ የሚገኘውን ያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካንም እንዲታደጉ ተጠየቀ፡፡

ለመስኖ ግድቦችና ለኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎች ትኩረት የሰጡ እንቅስቃሴዎች ተጀመሩ

የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ለመጀመርያ ጊዜ ‹‹የውኃ ኢነርጂ ትራንስፎርሜሽን ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ ተስፋ›› በሚል ርዕስ ሰኞ ሰኔ 10 ቀን 2011 ዓ.ም. ማክበር በጀመረው የውኃ ሳምንት፣ በውኃና ኢነርጂ ዘርፍ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይቶች መካሄድ ጀመሩ፡፡ በውይይቱ ትኩረት ይደረግባቸዋል ከተባሉት መካከል ከዚህ ዓመት ጀምሮ በሰፊው ስለሚገባበት የመስኖ ግድቦችና የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች፣ በተለይም የታላቁ የህዳሴ ግድብና የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ግድብ ተጠቃሾች ናቸው፡፡

ታሪካዊውን ቡፌ ደ ላጋር ማፍረስ ተጀመረ  

በለገሃር መልሶ ማልማት ፕሮጀክት ሳይት ላይ የሚገኘው ታሪካዊውና ዕድሜ ጠገቡ ቡፌ ደ ላጋር እንዳይፈርስ ከፍተኛ ጥረት ቢደረግም፣ የሚታደገው ሳያገኝ ዓርብ ሰኔ 7 ቀን 2011 ዓ.ም. አመሻሽ ላይ መፍረስ ጀምሯል፡፡

 ብሔራዊ ባንክ በዓይነት ለሚገኝ የውጭ ብድር መመርያ አወጣ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ግንቦት 28 ቀን 2011 ዓ.ም. በዓይነት ለሚገኝ የውጭ ብድር መመርያ አወጣ ነው፡፡ በዓይነት የሚገኝ የውጭ ብድር (External Loan in Kind) መመርያ ቁጥር FXD/61/2019 ተግባራዊ እንዲሆን ለሁሉም ባንኮች ተልኳል፡፡

በግልና በመንግሥት አጋርነት በኃይል ማመንጫ ለመሰማራት የውጭ ኩባንያዎች ፍላጎት እያሳዩ ነው

ከውጭ የፋይናንስ ምንጮች ከፍተኛ ብድር ያገኘው የኢትዮጵያ መንግሥት እንደተለመደው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎችን በራሱ አቅም መገንባት የሚችልበት አቋም ላይ ባለመሆኑ፣ የጀመረው የግልና የመንግሥት አጋርነት ፕሮግራም የውጭ ኩባንያዎችን ትኩረት እየሳበ ነው፡፡

የማዳበሪያ ግዥ በዕቅድ እየተከናወነ ባለመሆኑ ሌሎች ዕቃዎች በወደብ መከማቸታቸው ጥያቄ አስነሳ

በኢትዮጵያ የሚገኙ ከ380 እስከ 400 ኩንታል የሚጭኑ ከባድ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች በሙሉ ከጂቡቲ ወደብ ማዳበሪያ እንዲያነሱ ብሔራዊ ግዳጅ የተሰጣቸው በመሆኑ፣ ሌሎች በርካታ ዕቃዎች ወደብ ላይ በመከማቸታቸው ጥያቄ ቀረበ፡፡

የወንጀል ተጠርጣሪዎችን ለሕግ የሚያቀርብ ግብረ ኃይል ተቋቋመ

ዓርብ ግንቦት 30 ቀን 2011 ዓ.ም. ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) በተገኙበት በተካሄደ የጥበብ ምሽት፣ በከተማው ውስጥ የለየለት ዘረፋ መባባሱን የሚገልጽ ሒሳዊ መጠይቅ በቀረበባቸው ማግሥት፣ የወንጀል ተጠርጣሪዎችን ለሕግ የሚያቀርብ ግብረ ኃይል ተቋቋመ፡፡

ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ከይዞታቸው የሚነሱ የሚስተናገዱበት ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

ለሕዝብ ጥቅም ሲባል መሬት የሚለቀቅበትን፣ ካሳ የሚከፈልበትንና ተፈናቃዮች በድጋሚ የሚቋቋሙበትን የሚደነግግ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ፡፡

Popular