Friday, April 19, 2024

Author Name

የማነ ናግሽ

Total Articles by the Author

158 ARTICLE

የግዕዝ ቁጭት

በዘመኑ በዓለም ከነበሩት ኃያላን መንግሥታት አንዱ ቀዳሚ የነበረው የአክሱም ዘመነ መንግሥት፣ በሥልጣኔው ጫፍ የነካ እንደነበር ቢወሳም፣ እስከዛሬ የአክሱም ነገረ-ሥልጣኔ ከአምስት በመቶ በላይ አለመጠናቱን ተመራማሪዎች ይናገራሉ፡፡ በተለይ በሥነ ሕንፃ፣ ሥነ መድኃኒት፣ ቅርጻ ቅርጽ፣ አስተዳደር፣ የሥልጣን ሽግግር፣ የሥነ ከዋክብት፣ ንግድና እርሻ፣ የባህር ላይ እንቅስቃሴ ጫፍ ለነካው ለዘመኑ ቴክኖሎጂም ግራ የሚያጋቡ እንደሆኑ ምርምሮች ያመለክታሉ፡፡

በኤርትራ ላይ የተጣለው ማዕቀብ መጣሱ እንዲጣራ የፀጥታው ምክር ቤት ወሰነ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የፀጥታው ምክር ቤት በተደጋጋሚ በኤርትራ ላይ የተጣለው ማዕቀብ ተፈጻሚነትን በተመለከተ ምርመራ እንዲደረግ መወሰኑ ተገለጸ፡፡

የሶማሊያ አዲሱ ፕሬዚዳንት የኢትዮጵያ ጉብኝትና የሁለት አገሮች የወደፊት ተስፋ

ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ የሦስት ቀናት ጉብኝት ያደረጉት አዲሱ የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት መሐመድ አብዱላሂ ፎርማጆ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጋር ሽብርተኝነትን ለመዋጋትና የአገሪቱን የጦር ኃይል ለማጠናከር ስምምነት አድርገዋል፡፡

ሁለተኛው የሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሐ ግብር ለተግባር የቀረበ ይሆን?

የበፊቷን ኢትዮጵያ ገጽታ ከመሠረቷ ይቀይራል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ሕገ መንግሥት ተረቅቆ በ1987 ዓ.ም. መፅደቁ ይታወሳል፡፡

የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የዲፕሎማሲ አጭር ሥልጠና ሊሰጡ ይመጣሉ

የእስራኤል መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አማኑኤል ናህሾን፣ ለኢትዮጵያ ዲፕሎማቶችና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሠራተኞች በፐብሊክ ዲፕሎማሲ ላይ አጭር ሥልጠና ሊሰጡ እንደሆነ ታወቀ፡፡

የሳዑዲ ተመላሾችን መልሶ ለማቋቋም ፌዴራል መንግሥትና ክልሎች ተቀናጅተው እንዲሠሩ ተጠየቀ

ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ አገራቸው የሚመለሱ ዜጎች ያላንዳች እንግልት ወደ ቀያቸው ለመመለስና መልሶ ለማቋቋም፣ የፌዴራል መንግሥትና ክልሎች ተቀናጅተው እንዲሠሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ(ዶ/ር) ጠየቁ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከግብፅ ፕሬዚዳንት ጋር የጋራ መተማመን መፍጠራቸው ተነገረ

ሁለቱም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በወር ሁለት ጊዜ ለመገናኘት ወስነዋል ሽብርተኛነት የጋራ ጠላት መሆኑን መተማመናቸው ተገልጿል ግብፅ ኢትዮጵያን የሚጎዳ ማናቸውም ድርጊት አትፈጽምም ተብሏል

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከግብፅ ባለሥልጣናት ጋር ሊመክሩ ነው

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ከግብፅ ባለሥልጣናት ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሊመክሩ እንደሆነ ታወቀ።

Popular