Friday, March 1, 2024

Author Name

ዘመኑ ተናኘ

Total Articles by the Author

262 ARTICLE

ብሔራዊ መግባባት እንዴት?

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በታኅሳስ ወር 2010 ዓ.ም. ለአሥራ ሰባት ቀናት አድርጎት በነበረው ስብሰባ የውስጠ ድርጅት ዴሞክራሲ ችግር እንደነበረበት፣ ይኼም ችግር የሕዝብን መብት በማክበርና ተገቢውን አገልግሎት በመስጠት ረገድ ውስንነቶች እንደነበሩ ባወጣው መግለጫ ጠቁሟል፡፡ መግለጫው አክሎም በአገሪቱ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በርከት ባሉ አካባቢዎች ሰላምና መረጋጋት እየደፈረሰ፣ ሁከት የዕለት ተዕለት ክስተት እየሆነ መምጣቱን አስታውቋል፡፡

ሰሜን ሸዋ ውስጥ በ43 ቤቶች ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ ሁለት ሰዎች ሞቱ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሚዳ ኦሮሞ ወረዳ እምቢበሎ ተብሎ በሚጠራው ቀበሌ በ43 ቤቶች ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ ሁለት ሰዎች ሞቱ፡፡ ሦስት ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

‹‹የብሔር ጥያቄ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ገዥ አስተሳሰብ ሆኖ መቀጠል የለበትም››

አቶ ልደቱ አያሌው ባለፉት 26 ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ተሳትፎአቸው ይታወቃሉ፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲ ከማቋቋም ጀምሮ በአገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ጉልህ ሚና ተጫውተዋል፡፡ አገሪቱ ስላለችበት ወቅታዊ ሁኔታና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ከዘመኑ ተናኘ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡  

የግብፅና የሱዳን መሪዎች በህዳሴ ግድቡ ላይ መወያየታቸው በኢትዮጵያ ላይ የሚፈጥረው ሥጋት እንደሌለ ተነገረ

የግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲና የሱዳን አቻቸው ኦማር ሐሰን አል በሽር በህዳሴ ግድቡ ላይ መወያየት፣ በኢትዮጵያ ላይ ሥጋት እንደማይፈጥር መንግሥት አስታወቀ፡፡

‹‹የሕገወጥ መሣሪያ ዝውውር እየተበራከተ የመጣበት ዋነኛ ምክንያት በአገር ውስጥ ያለውን የሁከትና ግርግር እቅስቃሴ በጦር መሣሪያ ለማስደገፍ ታልሞ ነው››

በኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አንድ ወር አስቆጥሯል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የሰላመ መደፍረስ ተስተውሏል፡፡ በተፈጠረው ቀውስ ሳቢያም ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ዜጎች ለሞትና ለአካል ጉዳት ተዳርገዋል፡፡ እንዲሁም በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ዜጎች ከቀዬአቸው ተፈናቅለዋል፡፡

የወንድማሞቹ ስጦታ

አቶ ሙላት ፎጌ የአማጋ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ዋና ሥራ አስኪያጅ ናቸው፡፡ ድርጅታቸው በማምረት፣ በትራንስፖርትና በወጪና ገቢ፣ እንዲሁም በሌሎች የንግድ ዘርፎች ላይ የተሠማራ ድርጅት ነው፡፡ ድርጀቱም በቤተሰብ የተቋቋመ ነው፡፡ በጣና ሐይቅ ላይ የተንሰራፋውን የእንቦጭ አረም ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ድርጅታቸው ‹‹ለመጀመርያ ጊዜ›› የእንቦጭ አረም መከላከያ ማሽን ከቻይና ከሁለት ሚሊዮን ብር በመግዛት አገር ውስጥ አስገብቷል፡፡

የኢሕአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ተጀመረ

የኢሕአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ከማክሰኞ መጋቢት 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ መካሄድ ጀመረ፡፡ የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከመጋቢት 2 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በዝግ ሲመክር መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን፣ ስብሰባውን ሰኞ መጋቢት 10 ቀን 2010 ዓ.ም. አጠናቋል፡፡ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ግማሽ ቀን ዕረፍት ካደረጉ በኋላ የምክር ቤቱ ስብሰባ በዝግ መካሄድ ጀምሯል፡፡

የኢትዮጵያ ወቅታዊ ችግርና በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና የሚኖረው ተፅዕኖ

ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር ከሚሠሩ አገሮች አንዷ ነች፡፡ በሶማሊያ የመሸገውንና ራሱን ‹‹አልሸባብ›› ብሎ የሚጠራውን ቡድን ከመመከትና ከማዳከም ባሻገር፣ በሱዳንና በደቡብ ሱዳን መካከል ያለውን አለመግባባት ለመፍታት ከላይ ታች ስትል ነበር፡፡

ሦስቱ አገሮች ተቋርጦ በነበረው የህዳሴ ግድብ ላይ በካርቱም ሊወያዩ ነው

ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን ተቋርጦ በነበረው የህዳሴ ግድብ ላይ በካርቱም ውይይት ሊያደርጉ እንደሆነ ታወቀ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ሐሙስ መጋቢት 6 ቀን 2010 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ እንደተናገሩት፣ ሦስቱ አገሮች በህዳሴ ግድቡ ላይ የሚያደርጉት ውይይት ከመጋቢት 26 እስከ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. በካርቱም ይካሄዳል፡፡ 

የሕገወጥ መሳሪያዎች ዝውውር በስፋት መታየቱ ተገለጸ

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል አሰፋ አቢዮ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወቅት የሕገወጥ መሳሪያዎች ዝውውር በስፋት እንደታየ አስታወቁ፡፡ ኮሚሽነሩ ዛሬ መጋቢት 8 ቀን 2010 ዓ.ም....

Popular