Skip to main content
x

የሳምንቱ ገጠመኝ

አንዳንድ ትውስታዎች ያለንበትን ከባድ ጊዜ እያዋዙ የሚያስታውሱን ይመስለኛል፡፡ የውጭ ባለሀብቶችን ማማለልና መዋዕለ ንዋይ መሳብ የሚገባት አገር፣ የስግብግቦችና የአገር ፍቅር በውስጣቸው ያልሰረፀባቸው ሰዎች መጫወቻ ስትሆን እያየን ነው፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

ሁሌም ከቤቴ ስወጣ ፈጣሪዬን ‹‹በሰላም አውለኝ›› እላለሁ፡፡ ሰላም ከሌለ ምንም የለም፡፡ ሊኖር የሚችለው ውድመትና ዕልቂት ብቻ ነው፡፡ ማንም ጤነኛ ዜጋ ደግሞ ግጭትን፣ ውዝግብንና አላስፈላጊ ጠብን የሚጋብዝ ችግር ውስጥ ከመግባት ይልቅ በውይይትና በንግግር ችግሮችን መፍታትን ይመርጣል፡፡ ለዚህም ሲባል ነው ከጠብ ይልቅ ሰላም ስለሚያስፈልግ ‹‹ሰላም አውለኝ›› መባል ያለበት፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ቦሌ የሚያመራው ታክሲ ውስጥ ከጥቂት ተሳፋሪዎች ጋር ተቀምጠናል፡፡ ወያላው ‹‹ቦሌ! ቦሌ!›› እያለ ተጨማሪ ተሳፋሪዎች ሲጣራ፣ በዚህ መሀል ቁመተ ረዥምና ትከሻ ሰፊ ጎረምሳ ከአንዲት ቆንጆ ወጣት ጋር ገብተው ቦታቸውን ያዙ፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

ከ45 ዓመታት በኋላ ለማኅበራዊ ፍትሕ የተደረገው ትግል ትዝ ቢለኝ፣ ከአንድ ገጠመኜ ጋር ይህንን ትውስታ አያይዤ ለመጻፍ ተነሳሁ፡፡ ‹‹ያ ትውልድ›› ተብሎ የሚጠራው የ1960ዎቹ ወጣት የዘውድ አገዛዙን ለመገርሰስ ሲነሳ ካነገባቸው መፈክሮች መካከል ‹‹መሬት ላራሹ›› የሚባለው ታላቅ ሕዝባዊ መሠረት ነበረው፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

ባለፈው ሳምንት አንድ ጉዳይ ገጥሞኝ ወደ ሱልልታ ሄጄ ነበር፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሥጋና የጠጅ መናኸሪያ የሆነችውን ሱልልታ የፆም ቀን (ረቡዕ) ብሄድባትም፣ ጉዳዬን ከጨራረስኩ በኋላ ደስ የሚል መስተንግዶ አግኝቼባታለሁ፡፡ በተለይ በሥራ አጋጣሚ የተገናኘሁዋቸው የአካባቢው ሰዎች ትህትናና በጨዋነት የታጀበ አቀራረብ በጣም ነው ያስደሰተኝ፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

ከወቅቱ ትኩሳት ጋር የተያያዘ ገጠመኝ ነው፡፡ ባሳለፍነው ወር በአንዱ የሥራ ቀን ጠዋት በፐብሊክ ባስ የትራንስፖርት አገልግሎት ዓለም ባንክ ከሚባል ሠፈር ወደ ሜክሲኮ ተሳፍረን ትንሽ እንደተጓዝን፣ ከኋላዬ ካለ ወንበር አንድ ግለሰብ ከድምፁ እንደተረዳሁት ከሆነ በዕድሜ ወጣት ይመስለኛል በሞባይል ስልክ መነጋገር ጀመረ፡፡ ድምፁ ጎልቶ ይሰማ ነበር፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

የዚህ ዘመን አሳሳቢ ነገሮች ከመብዛታቸው የተነሳ የቱን አንስቼ የቱን ልተወው ያሰኛል፡፡ ያም ሆነ ይህ ከብዙዎቹ ጉዳዮች መካከል እኔ አንዱን ላነሳ ተገድጃለሁ፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

ወቅቱ የሠርግ ስለሆነ አንድ ትዝታዬን ልንገራችሁ፡፡ በአንድ ወቅት የተዋወቅኩት ሰው ወንድም ሠርግ ላይ የተገኘሁት በመኪናዬ ምክንያት ነው፡፡ ቀደም ሲል የደረሰኝ የሠርግ ካርድ ሆቴል የተዘጋጀ የምሣ ሥነ ሥርዓት ላይ ለመታደም ነበር፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

ሁለት ተቃራኒ ነገሮች ይኼንን ለመጻፍ መነሻ ሆነውኛል፡፡ የመጀመርያውን እንዲህ ልንገራችሁ፡፡ ለረጅም ዓመታት የሥራ ባልደረባዬ የሆነ አንድ ወዳጄ ሁለት ልጆቹን ወልዶ ካሳደገበት ቤት ልቀቅ መባሉን ነገረኝ፡፡ ቤት አከራዮቹ ቤቱን እንዲለቅ የነገሩት ባሳለፍነው ሳምንት ውስጥ ሲሆን፣ ምክንያታቸው ደግሞ ቤታቸውን ለመሸጥ በማሰባቸው ነው፡፡ ለበርካታ ዓመታት የኖረበት ቤት የኪራይ ዋጋው ከሌሎች ቤቶች ጋር ሲነፃፀር በጣም ጥሩ ነበር፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

ከዛሬ ስድስት ዓመት በፊት ከአዲስ አበባ ወደ ባህር ዳር የሚሄደውን አውሮፕላን ለመሳፈር ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የመጨረሻው ቦታ ላይ ደርሻለሁ፡፡ የአየር መንገዱ ሠራተኞች መንገደኞችን የሚያስተናግዱበት ሥፍራ ላይ ተቀምጬ ስጠባበቅ፣ ከዓመታት በፊት ዩኒቨርሲቲ አብረውኝ ከተማሩ ሁለት ሰዎች ጋር ተገናኘን፡፡