Wednesday, December 7, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisment -
  Category Template 49 – Pandemic PRO - NewsInBrief | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
  - Advertisment -

  ይድረስ ለሪፖርተር

  በዚህ ፈታኝ ጊዜ ከኢትዮጵያ ጎን እንቆማለን

  ሦስት የጃፓን ዜጎች በቅርቡ በኮሮና ቫይረስ እንደተያዙ ይታወቃል፡፡ ከእነዚህም በኋላ ሦስት ተጨማሪ ኬዞች እንደተገኙ ተገልጿል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ማዘኔን እየገለጽኩ ሁሉም የቫይረሱ ተጠቂዎች በፍጥነት እንዲያገግሙ እመኛለሁ፡፡

  አገር የሚያረጋጋ የሽግግር መንግሥት ይደንገግ

  ከአሁኑ ጊዜ ጀምሮ የኢሕአዴግ ወይም የብልፅግና ፓርቲ ሥልጣን ማብቂያ እስኪደርስ ድረስ ከእያንዳንዱ ፓርቲ የተውጣጡ፣ በውጭ የሚኖሩ፣ በዕውቀት የላቁና ተቀባይነቱ ያላቸው አካላት ኢትዮጵያን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ተረጋጋ መንገድ እንድትጓዝ ብሎም ከተለያዩ ችግሮች አውጥቶ ለሁሉም የምትበጅ አገር እንድትሆን ለማድረግ ሰላማዊ ሽግግር የሚያሰፍኑ የሊቃውንት ስብስብ ጊዜያዊ ሥልጣን ተረክበው አሁን ያለው መንግሥት ቆይታው በምርጫ እስከሚወሰንበት ጊዜ ድረስ ቦታውን ቢረከቡ መልካም ይሆናል፡፡ ይህንን የምልባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡

  የውጊያ አውድማ የመሰለችው የውሃን ግዛት

  ቤጂንግ ያለወትሮዋ ዝምታ ውጧታል፡፡ ለቤጂንግ ነዋሪዎች የዕለት ተዕለት መጓጓዧ የሆኑት አያሌ ብስክሌቶች ያለወትሯቸው በየመንገዱ ዳር በረዶ ተጋግሮባቸው ጫፍ እስከ ጫፍ ተሰድረዋል፡፡ በየመንገዱ ተፍተፍ የሚለው ልጅ አዋቂ ሁሉ በቤጂንግ ጎዳናዎች እንደቀድሞው አይታይም፡፡

  አንዳንዶቹ አገላለጾች ቢቃኑ

  የሪፖርተር ጋዜጣ የካቲት 8 ቀን 2012 ዓ.ም. ባወጣው ዕትሙ “የኢትዮጵያና የኦርቶዶክስ ታሪክ በመደበላለቁ እውነተኛው ታሪክ ተለይቶ እንዲነገር ተጠየቀ” በሚል ርዕስ የካቲት 5 ቀን 2012 ዓ.ም.

  ቀጣዩ ምርጫ ቀውስ እንዳያመጣ ከወዲሁ ይታሰብበት

  የእኔ ዕድሜ ዛሬ ከ60 ዓመት በላይ ሲሆን፣ ከልጅነቴ ጀምሮ በጎረቤታችን ሶማሊያ ከእርስ በርስ ጦርነት በቀር ስለልማት ሲወራ አልሰማሁም፡፡ ስለእነርሱ አገር ሰላም ዕጦት ስጨነቅ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አገራችን ኢትዮጵያም ከእነርሱ ብሳ ተገኝታለች፡፡

  ዳኞች በመመርያው አስፈላጊነትና ተግባራዊነት ላይ የጋራ ሐሳብ ይዘዋል

  ታኅሳስ 29 ቀን 2012 ዓ.ም. ዕትም ላይ ‹‹የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ክሶች ሒደት አስተዳደር መተግበሪያ መመርያ ረቂቅ ተግዳሮትና ተቃውሞ ገጠመው›› በሚል ርዕስ ዘገባ ማውጣታችሁ ይታወሳል፡፡

  ሁላችንም የሰላም ተሸላሚ ልንሆን ይገባል

  የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የኖቤል የሰላም ሽልማት ተሸላሚ መሆናቸው ለእሳቸውና ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ብቻ ሳይሆን፣ ለኢትዮጵያና ለኤርትራ ብሎም ለአፍሪካ ሕዝብ ኩራት ነው፡፡ ሰላም በናፈቃት ኢትዮጵያ የኖቤል የሰላም ሽልማት ተሸላሚ መሆን አስገራሚም አስደናቂም ነው፡፡ በአገር ውስጥ ተዘዋውሮ መኖር ባልተቻለበት፣ ሰዎች በየቦታው ንብረታቸው በሚዘረፍበት፣ በሚገደሉበት፣ ዘረኝነት በተስፋፋባት ኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ ለኖቤል የሰላም ሽልማት መብቃት ትልቅ ስኬት ነው፡፡

  የኢትዮ ኤርትራ የዕርቀ ሰላም ትሩፋት የዓለም የኖቤል የሰላም ሽልማት

  የኢትዮ ኤርትራ ዕርቀ ሰላም ምን ተገኘበት ብሎ መጠየቅ ተገቢነት ያለው ወቅታዊ ጥያቄ ነው፡፡ በአጠቃላይ በሁለቱም አገሮች በተፈጠረው አዲስ ግንኙነት በመሠረታዊነት ለሁለቱም ጎረቤት ሕዝቦች፣ ከዚህም በመለስ ለሁለቱም አገር መንግሥታት ከዲፕሎማሲ አንፃር ሲቃኝ እንዴት ይታያል? የተገኘው የሰላም ትርፍ (Peace Dividend) ምን ያህል ነው?

  ሰላም ሲመነዘር ስንት ያወጣ ይሆን?

  የአገራችን ሕዝቦች ለበርካታ ዓመታት አንዱ ከአንዱ ጋር በመከባበርና በመቻቻል የኖሩ በመሆናቸው ለዓለም ሕዝቦች ተምሳሌት ናቸው፡፡ አገራችን ኢትዮጵያ በቀዬአቸው ላሉት ዜጎች ብቻ ሳይሆን፣ በተለያዩ ምክንያቶች ባህር ማዶ ሄደው ኑሮን ለተያያዙትም በአካል ቢለዩም በሐሳብ ግን ቀንም ሆነ ሌሊት የምትናፈቅና ለክፉ ጊዜ ቀንም መሸሸጊያ የምትሆን ናት፡፡

  የሰላም አገር ወዴት ነች?

  ከሰሞኑ በአገራችን ሲሆን የታዘብነው ነገር ግራ ያጋባል፡፡ ጠብ ያለሽ በዳቦ አስመስሎብናል፡፡ አንፈልግህም የተባለው የመንግሥት አስተዳደር በአዲስ ተተክቶ፣ ዓለም ዕውቅና ሰጥቶት ገና ድክ ድክ ማለት ከመጀመሩ ያዙኝ ልቀቁኝ በማለት ሕዝብን ሰላም መንሳት፣ አልፎ ተርፎም በሰቆቃ የተሞሉ ዘግናኝ ግድያዎች ሲፈጸሙ ማየት በእውነት ምን እየሆንን ነው፣ ምን ዓይነት ዕብደት ነው ያሰኛል፡፡

  ከኪራይ ቤቶች ብልሹ አሠራር ማን ይታደገን?

  በደርግ ጊዜ የተወረሱ ቤቶችን እንዲያስተዳድር በአዋጅ የተቋቋመው የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት (ኪቤአድ)፣ በሰው ኃይል አደረጃጀቱ በርካታ ችግሮች ያሉበት ተቋም ነው፡፡ በተቋሙ በኃላፊነት የሚቀመጡት ግለሰቦች እንደየሥርዓቱ የፖለቲካ ቅኝት ሙስና በመፈጸምና በማስፈጸም አቅማቸው እንጂ የትምህርት ደረጃቸው፣ የሥራ ልምዳቸው ብቃታቸው ታሳቢ ተደርጎ አይደለም፡፡ በድርጅቱ ውስጥ ጥቂት ሙያተኞች በሚመጥናቸው ቦታ ቢመደቡም፣ ተደማጭነት አልነበራቸውም፡፡

  ለወሳኝ ችግሮቻችን የመፍትሔ ሐሳቦች!

  በበርካታ ውስብስብ ችግሮች ውስጥ የምትገኘው ኢትዮጵያ፣ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመፍጠር አመቺ ጊዜ ላይ ትገኛለች፡፡ በአዲሱ አመራር የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች አበረታች ቢሆኑም፣ አገራችን ያሉባት ውስብስብ ችግሮች በቀላሉ የሚፈቱ አይደሉም፡፡

  ለኢትዮጵያ ሰላም ሁላችንም ያለንን እናዋጣ!

  ሰላም የሁሉም ነገር መሠረት ነው፡፡ የሰላም ዋጋም እጅግ ውድ ነው ይባላል፡፡ ሰላም በሌለበት ነገሮችን ማከናወን እጅግ ከባድ ነው፡፡ ሰላም የሁሉ ነገር መሠረት በመሆኑም፣ በከፍተኛ ትኩረትና ጥንቃቄ ሊያዝ የሚገባ ነገር ነው፡፡

  የሜክሲኮና ኢትዮጲያ 70 ዓመታትን የተሻገረ ወዳጅነት

  በያዝነው ዓመት ሜክሲኮና ኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩበትን 70ኛ ዓመት ያከብራሉ። የዚህ ሳምንት የአዲስ አበባ ጉብኝቴ ዓላማም ይህን ወዳጅነት በማጠናከር በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የበለጠ ትስስር እንዲጎለብት የሚያስችሉ ሁኔታዎችን መፍጠር ነው።

  ይድረስ ለኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር

  በመጀመሪያ የማክበር ሰላምታችንን እያቀረብን የአቤቱታችንን ፍሬ ነገር እንደሚከተለው እናቀርባለን፡፡ በአዳማ ከተማ ቀበሌ 11 ውስጥ ልዩ ስሙ በሬቻ በሚባለው ሥፍራ ስፋቱ 8,728 ካሬ ሜትር ቦታ ከ19 ዓመታት በፊት የሊዝ አዋጁ ሳይወጣ በግዥ ወደ ድርጅት ሕጋዊ በሆነ መንገድ ተገቢው የአሹራ ክፍያ ተከናውኖ፣ ውሉም በአዳማ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ፀድቆ ስሙ ተዛውሮና ካርታውም በአይቤክስ ሆቴል ስም ተዘጋጅቶ ተሰጥቶን የቦታ ግብርም አንድም ሳይጓደል እስከ 2009 ዓ.ም. ድረስ ተጠናቆ ተከፍሏል፡፡ የየዓመቱም ክፍያ የተከናወነበት ደረሰኝ በእጃችን ላይ ይገኛል፡፡
  167,271FansLike
  250,620FollowersFollow
  12,400SubscribersSubscribe
  - Advertisment -
  - Advertisment -spot_img
  - Advertisment -
  Category Template 49 – Pandemic PRO - NewsInBrief | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

  ትኩስ ዜናዎች

  ትኩስ ዜናዎች እንዲደርሶ