Skip to main content
x

ይህች ቆሎ ካደረች አትቆረጠምም!

የሪፖርተር የእሑድ ዕትም መጋቢት 8 ቀን 2011 ዓ.ም. በፊት ገጹ ‹‹የአገሪቱ ባንኮች ለሦስት ፕሮጀክቶች ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ ሊያዋጡ ነው፤›› በሚል ርዕስ የጻፈውን ዘገባ አንብቤ በኩባንያ መልካም አስተዳደር ጥሰት ላይ የተሰማኝን ለመጻፍ ተገድጃለሁ፡፡

የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ክራሞቴ

ቃሊቲ ማረሚያ ቤት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሥር ከተቋቋሙ የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ መጣጥፌን ላቀርብ ያስገደደኝ በወቅቱ ስለሚነሱት የማረሚያ ቤቶች ችግር መሻሻል በቴሌቪዥንና በሬዲዮ የሚነገሩትን እዚያው ቃሊቲ ማረሚያ ቤት (ወህኒ) ቤት ለሁለት ወር በታሰርኩበት ጊዜ ያየኋቸውንና የሰማኋቸውን ለማስተማሪያነት ይሆኑ ዘንድ በማቅረብ ግዴታዬን ለመወጣት ነው፡፡ ‹‹ማን ይናገር የነበረ፣ ማን ያርዳ የቀበረ›› እንዲሉ አበው ነው፡፡

የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ አክሳሪነት የታየው በሜቴክና በክልሎች በተቋቋሙ ወርክሾፖች ብቻ ነው

ሪፖርተር በጥር 19 ቀን 2011 ዓ.ም. ዕትሙ ‹‹የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪን ለማስፋፋት በሊዝ ፋይናንስ የተጀመረው የማምረቻ መሣሪያዎች አቅርቦት ወደ ኪሳራ እያመራ መሆኑ ተገለጸ፤›› በሚል ርዕስ እንዲሁም የካቲት 17 ቀን 2011 ዓ.ም. ዕትሙ ‹‹ጀማሪ ኢንዱስትሪዎችን እንደሚያግዝ ተስፋ የተጣለበት የካፒታል ዕቃዎች ኪራይ አዋጅ ሊሻሻል ነው፤›› በሚል ርዕስ በፋይናንስ አምዳችሁ በተመሳሳይ ሪፖርተር ዜናዎችን መሥራታችሁ ይታወሳል፡፡

ከንቲባ ታከለ ኡማ የተበዝባዥ ሠራተኞች አቤቱታችን ይድረስዎ

ለክቡር ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ አቤቱታ የሚያቀርቡት ቁጥራቸው ከ300 ሺሕ በላይ የሆኑ ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ ከተማ የሆኑ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች፣ የሲቪል ሰርቪስ መሥሪያ ቤቶች፣ በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ቢሮዎችና ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቶች፣ በፌዴራል መሥሪያ ቤቶች የሹፍርና፣ የእንግዳ ተቀባይነት፣ የጥበቃ፣ የፅዳት፣ የአትክልት ክብካቤ ሥራ ላይ ተሠማርተው የቆዩ የቀድሞ ሠራተኛ ማኅበራት አመራሮች ናቸው፡፡

በ40/60 ቤቶች ጉዳይ ለሚመለከታችሁ አቤት እንላለን

በመጀመርያ በአገሪቱ እየተካሄዱ ላሉት ለውጦች ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) እንዲሁም ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) እና ሌሎችም በየደረጃው ያላችሁ መሪዎች መልካም ጅምሮችን በእናንተ በማየታችን ከሚደሰቱ ብዙኃን መካከል መሆናችንን በመግለጽ ወደ ጉዳያችን እንግባ፡፡

የአገራችን ‹‹ለውጥ›› ትርፍና ኪሳራው

ለውጥ የሚለውን ቃል፣ የአንድ ኅብረተሰብ የፖለቲካ ሥርዓት ወይም የመንግሥት መዋቅር በሌላ መተካት እንደሆነ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ባህሎች አካዳሚ የተዘጋጀው መዝገበ ቃላት (2000) በከፊል ይተረጉመዋል፡፡

የቀን ሕልም የሆነው የ40/60 ፕሮጀክት

በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መሪነት እየተተገበረ የሚገኘው ለውጥ አድናቂ ነኝ፡፡ አገራችን ወዳስከፊ ጎዳና እየተጓዘች የነበረችበትን መንገድ የእነ  ዓብይ (ዶ/ር) መምጣት ነገሮችን በሚያስደንቅ አኳኋን ወደ መልካም አቅጣጫ በመቀየር ላይ ይገኛል፡፡