Skip to main content
x

አንድነት ፓርቲ አዲስ አበባን ባለአደራ አካል እንዲያስተዳድራት ጠየቀ

አዲስ አበባ የሚያስተዳድራት አካል የሥራ ጊዜውን የጨረሰ በመሆኑ ባለድርሻ አካላትን ያካተተ ባለአደራ አስተዳደር እስከ ጠቅላላ ምርጫ ድረስ እንዲቋቋምና ይህም ተግባራዊ እንዲሆን፣ ከሌሎች የዴሞክራሲ ኃይሎች ጋር በጋራ በመሆን እንደሚታገል አንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት) አስታወቀ፡፡

የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ባለቤት የ11.3 ሚሊዮን ብር የፍትሐ ብሔር ክስ ተመሠረተባቸው

ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አንዱ የሆነው የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ባለቤት፣ የ11.3 ሚሊዮን ብር ዕዳ የፍትሐ ብሔር ክስ ተመሠረተባቸው፡፡ ከትምህርት ዘርፍ በተጨማሪ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ሥራዎች ላይ ተሰማርተው የሚገኙት፣ የዩኒቨርሲቲው ባለቤት አቶ ድንቁ ደያሳ የተከሰሱት፣ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 21ኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት ነው፡፡

በመንግሥት በብቸኝነት ተይዞ የቆየውን የቴሌኮም ገበያ ለውድድርና ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት የሚያደርግ ሕግ ሊወጣ ነው

በመንግሥት በባለቤትነት በብቸኝነት ተይዞ የቆየውን የቴሌኮም አገልግሎት ዘርፍ ለውድድር ክፍት የሚያደርግ፣ ማንኛውም የአገር ውስጥም ሆነ የውጭ የግል ኩባንያ ፈቃድ አውጥቶ በቴሌኮሙዩኒኬሽን አገልግሎቶች ውስጥ በጤናማ የውድድር መርህ መሳተፍ እንዲችል የሚፈቅድ ሕግ ተረቆ ለሕግ አውጪው ፓርላማ ተላከ።

በረጲ የደረቅ ቆሻሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አፈጻጸም ምክንያት ኃላፊዎች በሕግ ተጠያቂ ሊሆኑ ነው

ከሁለት ዓመታት በፊት መጠናቀቅ የነበረበት ረጲ የደረቅ ቆሻሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በመዘግየቱና ተጨማሪ ወጪ በማስከተሉ ምክንያት፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኃላፊዎችንና ኮንትራክተሩን የወሰደውን አካል በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ለኢቢሲ ቦርድ አመራር መንግሥት ዕጩዎችን የሚመርጥበት መሥፈርት ጥያቄ አስነሳ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) አዲስ የቦርድ ሰብሳቢና አባላትን ሹመት ጠንከር ካለ ክርክር በኋላ አፀደቀ፡፡ ነገር ግን መንግሥት ለቦርድ አመራር የሚመርጣቸውን ዕጩዎች የሚያቀርብበትን መሥፈርትና የትምህርት ዝግጅት ሊፈትሽ እንደሚገባ የምክር ቤቱ አባላት አሳስበዋል፡፡

የመኢአድ አመራሮች ልዩነታቸውን በመፍታት በጋራ ለመሥራት ተስማሙ

በመሀላቸው የነበረውን አለመግባባት በመፍታት ወቅቱ የሚጠይቀውን የፖለቲካ ቁመና በመላበስ በጋራ ለመሥራት መስማማታቸውን፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አመራሮች በጋራ በሰጡት መግለጫ አስታወቁ፡፡

እነ አቶ በረከት ስምዖን ፍርድ ቤት ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን እንዲያስከብርላቸው ጠየቁ

ከጥረት ኮርፖሬት ኩባንያዎች ጋር በተያያዘ በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ ታስረው የሚገኙት አቶ በረከት ስምዖንና አቶ ታደሰ ካሳ፣ ወደ ፍርድ ቤት ሲገቡና ሲወጡ ክብረ ነክ ስድብ እየተሰነዘረባቸው መሆኑን ገልጸው፣ ፍርድ ቤቱ ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን እንዲያስከብርላቸው ጠየቁ፡፡

ሃይኒከን ብሪወሪስ አክሲዮን ማኅበር የፍትሐ ብሔር ክስ ተመሠረተበት

ከስድስት ዓመታት በፊት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ነባር የቢራ ፋብሪካዎችን በመግዛትና አዳዲስ ፋብሪካዎችን በመገንባት፣ የተለያዩ የቢራ ዓይነቶችን በማምረት ላይ የሚገኘው ሃይኒከን ብሪወሪስ አክሲዮን ማኅበር የፍትሐ ብሔር ክስ ተመሠረተበት፡፡