Skip to main content
x

ማንባት ነው ያሰኘኝ

ማንባት ነው ያሰኘኝ
ማልቀስ ነው ያማረኝ

ከቁጭቴ ጋራ፤ ወትሮ ከመታገል
የንባ ማድጋዬን፤ ሰብሮ መገላገል
ማልቀስ ነው ያማረኝ፡፡

ያደራ ሳንዱቄ፤ ሲሰበር ክዳኑ
የባልንጀርነት፤ ሲጣስ ቃልኪዳኑ
መጋኛ ሲመታው
ዝምድና ሲከፋ
ፍቅር መሬት ከድታው
ባፍጢሙ ሲደፋ
የዳመነ ፊቴን፤ መዳፌ ውስጥ ልቅበር
የንባ ጋኔን ልስበር፡፡

‹‹ተውበሻል አሉ ተውበሻል. . .››

በደቡብ ኢትዮጵያ በቤንች ማጂ ዞን ከሚገኙ ብሔረሰቦች መካከል አንዱ የሆነው ሱርማ ከልዩ ልዩ መገለጫዎቹ አንዱ የተለየ የአለባበስ ባህል ያለው መሆኑ ነው፡፡ ልጃገረዶች አለባበሳቸው ከፊል ዕርቃንነትን ያጀበ ነው፡፡ ስለሱርማ የባህል እሴቶች የጻፈችው ለምለም መንግሥቱ እንደገለጸችው፣ ብትኑን ጨርቅ ከአንድ ወገን ቋጥረው በአንደኛው እጃቸው መካከል በማስገባት ቋጠሮው በትከሻቸው ላይ እንዲውል ያደርጉታል፡፡ ጨርቁ ሙሉ ለሙሉ አካላቸውን አይሸፍነውም፡፡ ከውስጥ ምንም አይነት ልብስ አይጠቀሙም፡፡

የ1950ዎቹ ኢትዮጵያውያን ጄኔራሎች

በመጨረሻው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት (1923 - 1967) የጦር ኃይሎች ከፍተኛ ጄኔራል መኰንኖች መካከል ግንባር ቀደምቱ በፎቶው የሚታዩ ናቸው፡፡ ፎቶው ከ1953 ዓ.ም. የታኅሣሥ ግርግር በፊት የተነሳ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የአፋር ባህላዊ ቤቶች

በኅዳር ወር መጨረሻ በአፋር ክልል የሚከበረው 12ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ለእንግዶች ማረፊያ እንዲሆኑ የአፋርን ሕዝብ አኗኗርና ባህል እንዲያሳዩ ተደርገው የተሠሩት ባህላዊ ቤቶች 480 ናቸው፡፡

‹‹ከማን አንሼ››

ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ቦሌ መድኃኔዓለም አካባቢ ኤድና ሞል ፊት ለፊት የሚገኘውን አደባባይ ከመኪኖች ጋር እየተጋፉ ያለፉት አህዮች ናቸው፡፡ በአፀደ ሥጋ የሌለው ዕውቁ ደራሲ መንግሥቱ ገዳሙ ‹‹ከማን አንሼ›› የምትባል ቤሳ ልብወለድ ነበረችው፡፡ የፊት ሽፋኗ አህያ ሙሉ ሱፍ ከነሰደርያውና ካፖርት ደርባ፣ ባርኔጣ ደፍታ፣ መነጽር አጥልቃ ትታይበታለች፡፡

ዝንቅ

በድርቅና በግጦሽ እጦት ምክንያት ከአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ ተሰደው የነበሩ ሳላዎች ወደ መኖሪያቸው እየተመለሱ ይገኛሉ፡፡

ቀዳሚው የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት

በፋሺስት ኢጣሊያ በ1928 ዓ.ም. ሰማዕት ለሆኑት አቡነ ጴጥሮስ፣ ከ1933 ዓ.ም. ድል በኋላ በአዲስ አበባ የቆመው የመጀመርያው የመታሰቢያ ሐውልት በፎቶው (በ1941 ዓ.ም. የተነሳ) የሚታየው ነበር፡፡