Friday, December 1, 2023

ዝንቅ

- Advertisement -
- Advertisement -

ኃይሌ ገብረሥላሴ ለመጨረሻ ጊዜ በባዶ እግሩ የተወዳደረበት የዓምናው ታላቁ ሩጫ

የሚሄድ በርጋታ የሚሄድ በርጋታ ድምጹ ሳይሰማ የሚኖር ይመስላል ከሁሉ እየተስማማ

በተራራማ አካባቢዎች ተጠብቆ የኖረ ዕውቀት

ባለፉት መቶ ዘመናት በተራራማ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች የመኖሪያ አካባቢያቸው አመቺ ባይሆንም እንዴት ኑሯቸውን አሸንፈው እንደሚኖሩ ተምረዋል።

ትዝ አለኝ የጥንቱ…›› የድሮ ባቡሮችና ሐዲዳቸው በአዳማ ከተማ

ያለህበት የሥልጣኔ መናኸሪያ  የጥበባት መጠለያ ከጊዜ ሽርሸራ መከለያ

የአዲስ አበባ ጋሪ በጀሞ ሠፈር

   የፍቅር ጠበቃ ፍቅር ጠበቃ አለው፣ ዘብ የሚቆምለት፤ ትዝታው እንዳይሞት፣ የሚሟገትለት፡፡

የሠላሳ ዓመት ትዝታ

ከሠላሳ ዓመታት በፊት በጥር 1979 ዓ.ም.፣ ሦስቱን የኢትዮጵያ ሙዚቃ ቤተሰብ አባላት ያገናኘች ቅጽበት፡፡ በግራ ፍራንሲስ ፋልሴቶ፣ ‹‹የትዝታው ንጉሥ›› ማህሙድ አሕመድና የቀድሞው ታንጎ ሙዚቃ ቤት ባለቤት አሊ ታንጎ ይታያሉ፡፡ 

እህል ይዞ የተገለበጠው ተሽከርካሪ

የእርዳታ እህል ጭኖ መስከረም 24 ቀን 2009 ዓ.ም. በሐረር መንገድ ሲያመራ የነበረው ከባድ ተሽከርካሪ ከነተሳቢው ሒርና ከተማ መግቢያ ላይ የመገልበጥ አደጋ ደርሶበት ነበር፡፡

አፄ ዮሐንስና የዓለም መሪዎች በ1881 ዓ.ም.

ከ128 ዓመታት በፊት ከነበሩት የዓለም መንግሥታት በዋናነት ከሚጠቀሱት አንዷ ኢትዮጵያ ነበረች፡፡ በወቅቱ በግንባር ቀደምትነት ከሚወሱት 22 አገሮች ከአፍሪካ የተጠቀሱት ኢትዮጵያና ግብፅ ብቻ ናቸው፡፡

የዘንድሮው የመስቀል በዓል ደመራ መስከረም 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ሲከበር

አዲስ ዓመት ደመና ጭጋጉ ሲገፍለት በተራው ሲፈካ ሰማይ ምድሪቱ በቀለማት ህብር ስትደምቅ ስትሞሸር ባደይ አትምጪ ይቅርብሽ ከኔ አትምጪ ነገን ሰንቀሽ እሰይ መስከረም ጠባ አዲስ ቀን ነው ብለሽ ይልቁን… የውስጤ ዝናብ ሲያባራ የመንፈሴ ሰማይ ሲጠራ የልቤ አደይ ሲፈካ የተስፋ ፀሐዬ ስትበራ ያኔ ነይልኝ በሰኔ ነይልኝ ባምሌ ነሐሴው ነይልኝ ለእንቁጣጣሽ አዲስ ቀን አዲስ ዓመት ነው፡፡ ታዬ አስፋው፣ ‹‹ሐጢሾ›› (2008) * * * መኖሪያ ቤት ውስጥ የገባው ፔንጉዊን በቁጥጥር ሥር ዋለ በብዛት በደቡባዊ ንፍቀ ክበብ ውስጥ የሚገኙት ፔንጉዊኖች የሚኖሩት በውኃማ አካባቢዎች መሆኑ ይታወቃል፡፡ እንደ ዓሳና ሌሎች ባህር ውስጥ የሚገኙ እንስሳትና ነፍሳትን ይመገባሉ፡፡ በደቡብ አሜሪካ በሀምቦልት ግዛት ውስጥ የሚገኘው አንድ ፔንጉዊን ግን የተለመደውን ምግቡን ወደ ጐን ብሎ የሚበላ ነገር ፍለጋ ወደ አንድ መንደር አቀና፡፡ ምሽት ስለነበር ልብ ያለው አልነበረም፡፡ በአካባቢው ወደሚገኝ አንድ ቤትም ጐራ ይላል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው የቤቱ ባለቤት ከወደ ማድቤታቸው የዕቃ ካካታ መስማታቸው ሌባ ገብቷል የሚል ስሜት ነበር ያሳደረባቸው፡፡ በፍጥነት ወደ ማድቤታቸው ሲገቡ ግን ያልጠበቁት ነበር ያጋጠማቸው፡፡ ምግብ ፍለጋ ጐራ ያለውን ፔንጉዊን የአካባቢው ፖሊስ ክፍል ደርሶ ወደ ነበረበት መልሶታል፡፡ * * * አነጋጋሪዋ ተሳፋሪ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ አካባቢ በአውሮፕላን በሚደረግ ጉዞ መንደገኞች የተለያዩ ነገሮች ያጋጥማቸዋል፡፡ አጠገባቸው ከተቀመጠ ሰው ጋር ቃል ሳይነጋገሩ በረራውን የሚጨርሱ፣ ቦታ የማይበቃቸው ሌላም ሌላም የተለመዱ ገጠመኞች ናቸው፡፡ ከኪንሳንቲ ወደ ኬንታኪ ይበር በነበረው አውሮፕላን የታየው ግን ከዚህ የተለየ ነበር፡፡ ዘ ቴሌ ግራፍ እንዳስነበበው ባለፈው ሰኞ ወደ ኬንታኪ ሲበሩ ከነበሩ መንገደኞች መካከል አንደኛው ከጐኑ ባለው መቀመጫ ላይ አሻንጉሊት አስቀምጧል፡፡ ሁኔታው ያስገረማት ሣራ ኖቪክ የተሰኘችው አንዲት ሴትም ስለ ሁኔታው በትዊተር ገጿ አሰፈረች፡፡ ተከታዮቿም ሰውየውን እንደሚያውቁት፣ ከዚህ ቀደምም ባርባራ በሚል ስም ያወጣውን ፎርጂድ ፓስፖርት በመጠቀም እንደ ጓደኛው ለሚቆጥራት ለአሻንጉሊቱ የአየር ቲኬት እንደቆረጠ፣ ሁኔታው የደህንነት ሥጋት በመፍጠሩ ከፍተኛ ፍተሻ እንደተካሄደበትና ባርባራ አሻንጉሊቷ እንጂ ሌላ ሰው አለመሆኑን ደርሰውበት በዚህ እንደተቋጨ አስረዷት፡፡ ለሣራ መረጃውን ከሰጧት ተከታዮቿ መካከል አንደኛው የአሻንጉሊቷንና የሰውየውን ፎቶ በትዊተር ገጿ ላይ ለጥፎታል፡፡ * * * በኮኬይን የተሞላ ቦርሳውን ፖሊስ እንዲያፋልገው የጠየቀ በአደንዛዥ ዕፅ የተሞላ ቦርሳው የጠፋበት የ19 ዓመት ወጣት፣ የጠፋ ቦርሳውን ፖሊስ እንዲያፋልገው በጠየቀበት ቅጽበት በቁጥጥር ሥር ዋለ፡፡ የሲያትል ፖሊስ ዲፓርትመንትን ጠቅሶ ዩፒአይ እንዳሰፈረው፣ የጠፋውን የወጣቱን ቦርሳ ያገኘ ሰው፣ ቦርሳውን ለፖሊስ አስረክቦ ነበር፡፡ በቦርሳው ውስጥ አራት ትላልቅና 27 ትናንሽ እሽግ ኮኬይን፣ ጥቂት ማሪዋናና፣ ሰዎች ከሱስ ወይም ከሌላ ህመም ጋር ተያይዞ ጭንቀት ውስጥ ሲገቡ ሊያነቃቃ የሚችል 50 እንክብል መድኃኒት፣ የ19 ዓመቱ ወጣት መታወቂያና የእጅ ስልክም ነበር፡፡ ቦርሳ ጠፍቶብኛል ብሎ ፖሊስን የጠየቀው ወጣትም፣ በአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪነት በቁጥጥር ሥር ውሏል፡፡ * * * በመጥፋት ላይ ያሉት የዓለም ቅርሶች ዩኔስኮ በአያያዝ ችግርና በዕድሜ ብዛት በመጥፋት ላይ የሚገኙ ዘጠኝ የዓለም ቅርሶችን ዝርዝር አወጣ፡፡ ዘ ኢንዲፔንደንት እንዳቀረበው ሥጋት ውስጥ የገቡት ቅርሶች የሚከተሉት ናቸው፡፡ በፍሎሪዳ የሚገኘው ኤቨር ግላድስ ናሽናል ፓርክ የቀድሞ የኢየሩሳሌም ከተማና ግንቦች በአሜሪካ የሚገኘው ብሌይዝ ቤሪየር ሪፍ ሪሰርቭ ሲስተም የግብፁ አቡ ሜና የኢንዶኔዥያው ትሮፒካል ሬይን ፎረስት ሄሪቴጅ ኦፍ ሱማትራ የጆርጂያው ባጋርቲ ካቴድራልና ጄላቲ ገዳም በፔሩ የሚገኘው ቻንቻን የአርኪዮሎጂ ዞን በማዳጋስጋር የሚገኘው አስናና ደን በሊቨርፑል የምትገኘው ማሪታይም መርካንታይል ከተማ ናቸው፡፡

ቄንጠኛው የመጥረጊያና የመወልወያ ገበያ ሲኤምሲ የጋራ መኖሪያ ቤቶች አቅራቢያ

ኢትዮጵያዊ ነኝ!              (በድሉ ዋቅጅራ) ኢትዮጵያዊ ነኝ! በላሊበላ አስቀድሼ፣ ሸህ ሁሴን ባሌ የተገኘሁ፤ በአባ ገዳ ተመራርቄ፣ መካ ላይ እርስቅ ያገኘሁ፡፡

ድሬዳዋን በተደጋጋሚ የጐርፍ አደጋ ሲያጠቃት በመጀመሪያ ደረጃ ለአደጋ ተጋላጭ የነበረው አሸዋ ሜዳ ገበያ ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት ግን በተለያዩ ሥራዎች የከተማዋ የጐርፍ አደጋ ሥጋት ተቀርፏል፡፡* * *ኢዮሐ!ኢዮሐ!አበባ ፈነዳፀሐይ ወጣ ጮራዝናምዘንቦአባራ፡፡ዛፍ አብቦአፈራ፡፡ክረምት መጣ ሄደዘመን ተወለደ፡፡አዲስ ዓለም ሆነ፡፡ሌሊት ሊነጋጋ…ጋራው ድንጋይ ከሰል፣የተተረከከ ፍም እሳትደመናውፀሐይ ያነደደውዓለም ሞቆደምቆ፡፡ብርሃን ሲያሸበርቅጤዛው...
- Advertisement -

ትኩስ ፅሁፎች

ትኩስ ዜናዎች ለማግኘት